Central Ethiopia Regional State Justice Bureau https://www.cerjustice.gov.et/index.php/ en በ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ላይ አስተያየት ይስጡ! https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/203 በ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ላይ አስተያየት ይስጡ! Superadmin Thu, 07/09/2026 - 11:35

በ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ላይ አስተያየት ይስጡ!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት እያዘጋጃቸው ከሚገኙ ረቂቅ መመሪያዎች መካከል አንዱ የ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ነው።

ቢሮው ረቂቅ መመሪያውን ይበልጥ የተሟላና ጥራት ያለው ለማድረግ በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች ከሚሰበሰቡ ግብዓቶች በተጨማሪ፣ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ ገንቢ ሐሳቦችንና አስተያየቶችን በቢሮው ድረ ገጽ ፣ በቴሌግራም ገጽ እና በነፃ የጥሪ ማዕከል በ 8651 አማካኝነት ለመቀበል ይፈልጋል።
ስለሆነም በረቂቅ መመሪያው ላይ ያላችሁን ገንቢ ሐሳብና አስተያየት በተዘጋጁት መገናኛ አማራጮች እንድታደርሱን በአክብሮት እንጋብዛለን።

"የእርስዎ ገንቢ ሐሳብ የተሻለ የሕግ ሥርዓት ግንባታ አካል ነው!"
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ

Thu, 09 Jul 2026 08:35:07 +0000 Superadmin 203 at https://www.cerjustice.gov.et የዐቃቤ ህግ አስተዳደርን እና ሙያዊ አፈጻጸምን ለማጠናከር የተዘጋጁ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በማኔጅመንት ውይይት ግብዓት ተሰበሰበ https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/201 የዐቃቤ ህግ አስተዳደርን እና ሙያዊ አፈጻጸምን ለማጠናከር የተዘጋጁ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በማኔጅመንት ውይይት ግብዓት ተሰበሰበ Seble Wed, 07/08/2026 - 11:08

የዐቃቤ ህግ አስተዳደርን እና ሙያዊ አፈጻጸምን ለማጠናከር የተዘጋጁ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በማኔጅመንት ውይይት ግብዓት ተሰበሰበ******

ሀላባ፣ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም. የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቤ ህግ ተቋማዊ አስተዳደርን፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርንና የሥራ አፈጻጸምን የበለጠ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ውጤታማ ለማድረግ ያለሙ አራት ረቂቅ መመሪያዎችን ለማፅደቅ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ከቢሮው ኃላፊዎችና ከማኔጅመንት አባላት ጋር ለሁለት ቀናት የቆየ ዝርዝር ውይይት አካሂዷል።

በሰኔ 23 እና 24/2018 ዓ.ም. በሀላባ በተካሄደው የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ፣ የዐቃቤ ህግ ሥነ-ምግባር አፈጻጸም፣ የቅጥር፣ የምደባና የዝውውር አፈጻጸም፣ የዐቃቤ ህግ አስተዳደር ጉባኤ አባላት የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም የዐቃቤ ህግ የሥራ አፈጻጸም ምዘናን የሚመለከቱ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በዝርዝር ቀርበው ተመርምረዋል።

ረቂቅ መመሪያዎቹ አንቀጽ በአንቀጽ ከቀረቡ በኋላ የማኔጅመንት አባላት የመመሪያዎቹ ይዘት፣ ቅርጽና ተግባራዊነት የበለጠ እንዲጠናከር የሚያግዙ ገንቢ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርበዋል። በቀረቡት ሀሳቦች ላይም የረቂቅ አዘጋጅ ቡድኑ ዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱን የበለጠ ፍሬያማ አድርጎታል።
በመድረኩ የተሰበሰቡ ግብዓቶች እና ማሻሻያ ሀሳቦች በረቂቅ መመሪያዎቹ ውስጥ ተካተው የመጨረሻ ማስተካከያ እንዲደረግባቸውና ለፀደቃ ጉባኤ በሚቀርብ ደረጃ እንዲዘጋጁ የቢሮው ማኔጅመንት አቅጣጫ አስቀምጧል።

የፍትህ ቢሮው እነዚህ መመሪያዎች ሲፀድቁ በዐቃቤ ህግ አገልግሎት ውስጥ የሙያ ሥነ-ምግባርን፣ የሰው ኃይል አስተዳደርን፣ የአፈጻጸም ምዘናን እና ተቋማዊ አስተዳደርን በማጠናከር የፍትህ አገልግሎቱን ጥራትና ተጠያቂነት የበለጠ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በቀጣይ የሚዘጋጁ እና የሚፀድቁ ሌሎች መመሪያዎችም ተመሳሳይ ተሳትፎና ግብዓትን ማዕከል በማድረግ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

Image

Wed, 08 Jul 2026 08:08:29 +0000 Seble 201 at https://www.cerjustice.gov.et በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመግታት የህግ ማዕቀፍ ማጠናከር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/200 በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመግታት የህግ ማዕቀፍ ማጠናከር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ Seble Wed, 07/08/2026 - 11:06

በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመግታት የህግ ማዕቀፍ ማጠናከር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ
ሀላባ፣ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ HOPE FOR JUSTICE ከተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ኢ-መደበኛ ፍልሰትን፣ በሰው መነገድን እና ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ደንብ ቁጥር 32/2017 አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የHOPE FOR JUSTICE የፕሮግራሞች ዳይሬክተር አቶ ፈይሳ ተፈራ ሲሆኑ፣ የመክፈቻ ንግግሩን ያቀረቡት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ ናቸው።
አቶ አብርሃም በንግግራቸው እንደገለጹት፣ በሰው መነገድና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች በዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ሰብዓዊ መብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኙ ጠቅሰው፣ ችግሩን በህግ፣ በቅንጅት እና በህዝብ ተሳትፎ ለመከላከል የተጠናከረ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለውም፣ አዋጁና ደንቡ የሰው መነገድን፣ ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን እና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርን ለመከላከል እንዲሁም የፍልሰት አስተዳደርን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የህዝብ አደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት እና የሙያ ማህበራት በቅንጅት እንዲሰሩ የሚያግዝ የትብብር ሥርዓት መዘርጋቱን አስረድተዋል።
በክልሉ በተለይም በሀድያ፣ በከምባታ ጠምባሮ፣ በጉራጌ፣ በምዕራብ ጉራጌ፣ በስልጤ እና በሀላባ ዞኖች የሚስተዋሉ በሰው መነገድና ህገ-ወጥ ፍልሰት ችግሮችን ለመቀነስ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የክትትል እና የቅንጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል።
በመቀጠል ለውይይት የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው የፍልሰት ትብብር ጥምረት አስተባባሪ አቶ ታደሰ መንድሙ ሲሆኑ፣ በአዋጁና በደንቡ ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ ዐቃቤ ህጎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ችግሩን ለመከላከል የራሳቸውን ድርሻ በተጠናከረ መልኩ ለመወጣት ቁርጠኝነታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ህብረተሰቡም ከህገ-ወጥ የፍልሰት መንገዶች በመራቅ ህጋዊ አሰራሮችን መከተል እንደሚኖርበት ተገልጿል፡
በመጨረሻም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ እና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሀም በድሩ እና የHop for justce የፕሮግራሞች ዳይሬክተር አቶ ፈይሳ ተፈራ በማጠቃለያ ንግግራቸው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክተዋል።

Image

Wed, 08 Jul 2026 08:06:00 +0000 Seble 200 at https://www.cerjustice.gov.et የሥራ ሥነ-ምግባር ግንባታ ለተቋማት ውጤታማነትና ለተገልጋይ እርካታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/199 የሥራ ሥነ-ምግባር ግንባታ ለተቋማት ውጤታማነትና ለተገልጋይ እርካታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ Seble Wed, 07/08/2026 - 11:03

የሥራ ሥነ-ምግባር ግንባታ ለተቋማት ውጤታማነትና ለተገልጋይ እርካታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ሀላባ፣ ሰኔ 2/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ለቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች በሥራ ሥነ-ምግባር ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ፣ የሥራ ሥነ-ምግባር በታታሪነት፣ በተጠያቂነትና በቁርጠኝነት ሥራን በመከወን የሚረዳ መሠረታዊ እሴት መሆኑን ገልፀው፣ ተቋማት ተልዕኳቸውን በተሳካ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችላቸው ዋና መሠረት መሆኑን አስረድተዋል።
አቶ አብርሃም አክለውም በፍጥነት እያደገ የመጣውን የተገልጋዮች ፍላጎት  ለማሟላት ሠራተኞች ከፍተኛ የሥራ ሥነ-ምግባር ሊላበሱ እንደሚገባ ገልፀዋል። ጥሩ የሥራ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሠራተኞች ለከፍተኛ ኃላፊነትና ለሥራ ዕድገት እንደሚመረጡ ሲገልጹ፣ የሥራ ሥነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸው ሠራተኞች የተቋማትን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት እንቅፋት እንደሚሆኑ አስገንዝበዋል።
በስልጠናው ላይ የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስነ-ምግባር አውታሮች ማስተባበር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልሽኩር ቡሴር በሥራ ሥነ-ምግባር፣ በተጠያቂነት፣ በሙያዊ ታማኝነት፣  እና በተገልጋይ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ዝርዝር ገለፃ አቅርበዋል።
በስልጠናው ወቅት ተቋማት ውጤታማና ትርፋማ ለመሆን የሰው ሀብታቸውን በዕውቀትና በክህሎት ብቻ ሳይሆን በጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባር ማነጽ እንደሚገባቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ኢ-ሥነ-ምግባራዊ ድርጊቶችና ሙስና በተቋማት ውስጥ የውጤታማነትና የተገልጋይ እርካታ መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።
በውይይቱ ወቅት ተሳታፊዎች የሥራ ሥነ-ምግባር በተቋማት ውስጥ ጠንካራ የአገልግሎት ባህል ለመፍጠር፣ የተገልጋዮችን እምነት ለማጠናከርና የሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል። ስልጠናው በየዕለቱ በሥራ ቦታ የሚያጋጥሙ የሥነ-ምግባር ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ጠቃሚ ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸውም ገልፀዋል።
በተለይም ተሳታፊዎቹ ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በተግባር በመተርጎም ተገልጋይ ተኮር፣ ተጠያቂና ግልጽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
ስልጠናው በተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት የታጀበ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ተጠናቋል።

Image

Wed, 08 Jul 2026 08:03:28 +0000 Seble 199 at https://www.cerjustice.gov.et የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 እና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ የዐቃቢያነ ህግ አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተካሄደ https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/198 የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 እና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ የዐቃቢያነ ህግ አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተካሄደ Seble Wed, 07/08/2026 - 10:57

የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 እና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ የዐቃቢያነ ህግ አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተካሄደ

ሀላባ፣ ግንቦት 15/ 2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 እና በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የዐቃቢያነ ህግ ሚናን ለማጠናከር ያለመ ሥልጠና ለክልሉ፣ ለዞን እና ለልዩ ወረዳ ዐቃቢያነ ህጎች በሆሳዕና ከተማ ለሁለት  ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ ።

በሥልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የኮርፖሬት ዘርፍ  ኃላፊ  አቶ ሰላሙ ዳንኤል  በንግግራቸው  የሕግ የበላይነት እውን እንዲሆን በወንጀልና በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የሚፈፀሙ ተግባራት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸው፣ በተለይም ቅጣቶች በፍትሃዊነት፣ በወጥነትና በሕግ መሠረት እንዲወሰኑ የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።
በሥልጠናው ወቅት ዐቃቢያነ ህግ በወንጀል ቅጣት አወሳሰን ሂደት ተገቢ የቅጣት አስተያየት በመስጠት የፍትህ ሥርዓቱን ወጥነትና ተዓማኒነት በማስጠበቅ ያላቸው ሚና በስፋት ተዳሷል።
በተጨማሪም በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ፣ የግዥ ውሎችና ሌሎች የመንግስት ጉዳዮች በሕግ መሠረት እንዲፈፀሙ እንዲሁም ከህገ-ወጥ ተግባራትና ከኪሳራ ለመከላከል የዐቃቢያነ ህግ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተጠቅሷል።
በመድረኩ ላይ በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ በክልሉ ዐቃቤ ሕግ በአቶ ደጀኔ ማቲዎስ የቀረበ ሲሆን፣ በፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍትሕ አስተዳደር የዐቃቤ ሕግ ሚናን የተመለከተ ጽሑፍ ደግሞ በዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ በአቶ አሊ ሰይድ አማካኝነት ቀርቧል።
ሥልጠናው የሙያ ብቃትን ለማሳደግ፣ ወጥ አሰራርን ለማጠናከር እና የፍትህ አገልግሎትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው  ተገልጿል።
ተሳታፊዎችም በሥልጠናው የሚቀርቡ ሐሳቦችን በጥልቀት በመከታተልና ልምድ በመጋራት የተሻለ የፍትህ አገልግሎት ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

Image

Wed, 08 Jul 2026 07:57:31 +0000 Seble 198 at https://www.cerjustice.gov.et ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ኢ-መደበኛ ፍልሰትና በሰው መነገድ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማዕቀፍ ማጠናከርን ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሄደ https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/197 ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ኢ-መደበኛ ፍልሰትና በሰው መነገድ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማዕቀፍ ማጠናከርን ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሄደ Seble Wed, 05/13/2026 - 09:25

ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ኢ-መደበኛ ፍልሰትና በሰው መነገድ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማዕቀፍ ማጠናከርን ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ሀላባ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ኢ-መደበኛ ፍልሰትን፣ በሰው መነገድን እና ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ደንብ ቁጥር 32/2017 አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ እና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ ሲሆኑ በንግግራቸው እንደገለጹት :- በሰው መነገድና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች በዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ሰብዓዊ መብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ እና ችግሩን በህግ፣ በቅንጅትና በህዝብ ተሳትፎ ለመከላከል የተጠናከረ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው በማከልም አዋጁና ደንቡ የሰው መነገድን፣ ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን እና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርን ለመከላከል እንዲሁም የፍልሰት አስተዳደርን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸው ተጠቁሟል። በተለይም የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የህዝብ አደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት እና የሙያ ማህበራት በቅንጅት እንዲሰሩ የሚያግዝ የትብብር ሥርዓት መዘርጋቱንም ገልጸዋል።
በክልሉ በተለይም በሀድያ፣ በከምባታ ጠምባሮ፣ በጉራጌ፣ በምዕራብ ጉራጌ፣ በስልጤ እና በሀላባ ዞኖች የሚስተዋሉ በሰው መነገድና ህገ-ወጥ ፍልሰት ችግሮችን ለመቀነስ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የክትትልና የቅንጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንም ጠቅሰዋል።
በመቀጠልም ለውይይት የተዘጋጀውን ሠነድ በጥሩ ሁኔታ በማቅረብ ስልጠናውን የሰጡት የቢሮው ዐቃቤ ህግ አቶ ጢሞትዮስ ዋርጎ እና የቢሮው የፍልት ጥብብር ጥምረት አስተባባሪ አቶ ታደሰ ወንድሙ ሲሆኑ

በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች፣ ፈፃሚዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ችግሩን ለመከላከል የራሳቸውን ድርሻ በተጠናከረ መልኩ ለመወጣት ቁርጠኝነታቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ህብረተሰቡም ከህገ-ወጥ የፍልሰት መንገዶች እንዲርቅ እና ህጋዊ አሰራሮችን እንዲከተል ጥሪ ቀርቧል።

ፍቅርተ ዘለቀ

የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን

Image

Wed, 13 May 2026 06:25:43 +0000 Seble 197 at https://www.cerjustice.gov.et በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ። https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/196 በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ። Seble Fri, 05/01/2026 - 00:11

በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ።

ሚያዝያ  20 / 2018 ዓ.ም ሀላባ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ድርጊቱ ሲፈፀም ፈጣንና ፍትሃዊ ምላሽ ለመስጠት ያለመ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወራቤ ከተማ ተሰጠ።

በሥልጠናው  በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በተለይ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ-እድሜ ጋብቻን ለመከላከል እና ተፈጽሞ ሲገኝ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የሚሰሩ ዐቃቤያነ-ህጎች፣ መርማሪ ፖሊሶች እና የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ መድረኩን ያስጀመሩት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ አክመል አህመዲን ሲሆኑ በንግግራቸውም
ቢሮው ለሴቶችና ህፃናት መብትና ደህንነት ልዩ ትኩረት በመስጠት ከክልል እስከ ታችኛው የፍትህ መዋቅር ድረስ የተደራጀ የሥራ  ክፍል እንዲደራጅ በማድረግ ባለሙያዎችን በመመደብ የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው አያይዘው በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ የጥቃት ድርጊቶቹ በብዛት የሚፈፀሙባቸውን አካባቢዎች በመለየት ከUNICEF ጋር በመተባበር የበጀት፣ የቁሳቁስ እና የሥልጠና ድጋፎችን እየሰጠ ቢሆንም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት እንደ ሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ሥልጠናው በተለይ በመጋቢት 24/2018 ዓ.ም የፀደቀው አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ (አዋጅ ቁጥር 1410/2018) ላይ ትኩረት በመስጠት ተሳታፊዎች ዲጅታል ማስረጃዎችን እና ዘመናዊ የምርመራ ስልቶችን በተግባር እንዲጠቀሙ  አሳስበዋል።

ኃላፊው በማከልም ተሳታፊዎች የጉዳዩን አሳሳቢነትና ውስብስብነት በጥልቀት እንዲገነዘቡ እና በሥልጠናው የሚገኙ ክህሎቶችን በተግባር በማዋል በመረጃ አያያዝና በአላላክ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም
የሴቶችና ህፃናትን መብት የሚጎዱ አካላትን በህግ አግባብ ተጠያቂ በማድረግ አስተማሪ ውሳኔዎች እንዲሰጡ እና ሁለንተናዊ ጥበቃ እንዲረጋገጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በመቀጠልም ለሥልጠናው የተዘጋጀው ሰነድ በቢሮው  ዐቃቤ ህግ በአቶ ጢሞትዮስ ዋርጎ ቀርቦ ተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ  አድርገውበታል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች ባነሷቸው ሀሳቦች ላይ የቢሮው የሴ/ህ ልዩ የም/ ክስ ጉ/ ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አፈወርቅ ደሚሴ እና በአቶ ጢሞትዮስ ዋርጎ ምላሽና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን፤ የሚታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል ሁሉም አካል የሚጠበቅበትን ተግባር በመከወንና ተቀናጅቶ ለመስራት በመዘጋጀት  ፍትሕ እንዲረጋገጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ በማቅረብ የማጠቃለያ ሀሳቦች ተሰጥተው  መድረኩ ተጠናቋል።

የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን

Image

Thu, 30 Apr 2026 21:11:38 +0000 Seble 196 at https://www.cerjustice.gov.et የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገመገመ። https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/195 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገመገመ። Seble Mon, 04/20/2026 - 10:43

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገመገመ።
ሀላባ፣ ሚያዚያ 8/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከአመራሮችና ከማናጅመንት አካላት ጋር በመሆን በጥልቀት ገምግሟል።
በዚሁ የግምገማ መድረክ የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን የተገኙ ሲሆን፣ የ9 ወራት አፈፃፀም ሪፖርቱ በልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ፍቅሩ በተደራጀ ሁኔታ ቀርቧል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ አመራሮችና ማናጅመንት አባላት ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ጠንካራ አፈፃፀሞችን እና የሚሻሻሉ ዘርፎችን ለይተው ገንቢ አስተያየት አቀርበዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በግልፅ በማብራራት፣ በተለይም የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከር እና የታዩ ድክመቶችን በተግባር ማሻሻል ላይ እንዲተኮር አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን

Image

Mon, 20 Apr 2026 07:43:09 +0000 Seble 195 at https://www.cerjustice.gov.et የ 2018 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/194 የ 2018 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።  Seble Thu, 03/26/2026 - 09:53

የ 2018 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ
ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

መጋቢት:-15 /2018 ዓ.ም

የክልሉ ፍትህ ቢሮ በምርጫ ህግ ፤ በጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ በቡታጀራ ከተማ  አካሂዷል።

በመርሀ ግብሩም ከዞንና ከልዩ ወረዳ ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ ከፍትሕ መምሪያዎች የተወከሉ ዓቃቢያነ ሕግ፣ ከፖሊስ መምሪያዎች የተገኙ መርማሪ ፖሊሶች እና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ እና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ እንደገለፁት፣ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው 7ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የዜጎች የሥልጣን ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፍትሕ ተቋማት ብስለትና ዝግጁነት የሚፈተንበት  ወቅት ነው።

ምርጫ የነፃነት መግለጫ መሆን እንጂ የሁከት ምንጭ መሆን እንደማይገባም አጠናክረው  ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ዳኞች ገለልተኛና ፈጣን ውሳኔ መስጠት፣ ዓቃቢያነ ሕግ የሕግና የሕዝብ ጥበቃን ማረጋገጥ፣ መርማሪ ፖሊሶችም ጥሰቶችን በፕሮፌሽናል መንገድ መመርመር እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በመድረኩ ከተነሱ አንዱ ዋና ጉዳይ ደግሞ በቴክኖሎጂ የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና ሐሰተኛ መረጃዎች በምርጫ ሂደት ላይ የሚያሳድሩት አደጋ ነበር።

እነዚህ ድርጊቶች የሕዝብ እምነትን ሊያበላሹና ሰላማዊ ምርጫን ሊያደናቅፉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በመሆኑም የፍትሕ አካላት የነጻ አስተያየት መብትን እያከበሩ፣ ነገር ግን ሀገርና ሰላምን የሚያናጋ የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭትን በሕግ መቆጣጠር እንዳለባቸው ተነግሯል፣ የሲቪክ ማኅበራትም ሕዝቡን በማንቃት፣ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በማስተማርና ሂደቱን በቅርብ በመከታተል ትልቅ ሚና መጫወት እንዳላቸው ተገልጿል።

በመድረኩም በቢሮው ዐቃቤ ህግ በአቶ ጢሞትዮስ ዋርጎ እና በአቶ ደረጀ ደስታ የመወያያ ሰነዶች ቀርበው ተሳታፈዎች ጥልቅ ውይይት አድርገውበታል

በመጨረሻም መድረኩም ተሳታፊዎች ልምድ የሚለዋወጡበት፣ ሕጋዊ አሰራሮችን የሚያጠናከሩበት እና ለምርጫው ስኬት በአንድነት ለመስራት ቃል የሚገቡበት መሆን እንደሚገባው ተገልጿል።

Image

Thu, 26 Mar 2026 06:53:19 +0000 Seble 194 at https://www.cerjustice.gov.et የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ -ህግ የሙያ ሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ለማሻሻል ከቢሮው ዐቃቢያነ ህጎች ጋር ውይይት አደረገ። https://www.cerjustice.gov.et/index.php/node/193 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ -ህግ የሙያ ሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ለማሻሻል ከቢሮው ዐቃቢያነ ህጎች ጋር ውይይት አደረገ። Seble Wed, 03/11/2026 - 10:14

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ -ህግ የሙያ ሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ለማሻሻል ከቢሮው ዐቃቢያነ ህጎች ጋር ውይይት አደረገ።

ሀላባ መጋቢት 1/2018 ዓ.ም

ቢሮው የ0ቃ ቢያነ - ህግ የሙያ ሥነ - ምግባር ረቂቅ መመሪያን በማዘጋጀት ከቢሮው ዐቃቤ ህጎች ጋር በመወያየት ረቂቁን በተሻለ ለማጎልበት አጋዥ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለማግኘት በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ከተወያይዎች ጠቃሚና ገንቢ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ረቂቁን ባዘጋጁት ቡድኖችም ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ረቂቁን በቀጣይ ለማሻሻል ወሳኝ ግብዓቶች ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

ለዘገባው የቢሮው መ/ኮ

Image

Wed, 11 Mar 2026 07:14:06 +0000 Seble 193 at https://www.cerjustice.gov.et