Central Ethiopia Regional State Justice Bureau https://www.cerjustice.gov.et/ en በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል እንደሆነ ተገለጸ። https://www.cerjustice.gov.et/node/184 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል እንደሆነ ተገለጸ። Seble Mon, 09/08/2025 - 11:40

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል እንደሆነ ተገለጸ።

ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ  የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ/ም ዕቅድ የሚመክር ጉባኤ በቡታጅራ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው “የህግ የበላይነትና ሰብዓዊ ክብር ያረጋገጠ የፍትህ ስርዓት እንገነባለን!” በሚል መሪ ቃል ነው  ከሴክተሩ አመራር፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከህዝብ ክንፍ አባላት እየተካሄደ የሚገኘው።

አቶ አክመል አህመዲን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል በመደረጉ በሴክተሩ በተሰሩ ስራዎች ላይ ከፍ ያለ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን ገልጸዋል።

ባለፈው በጀት አመት የክልሉ ሰላም የተረጋጋ እንዲሆን ግጭት አባባሽ ማህበራዊ ሚዲያዎች አደብ እንዲገዙ ፣ በርካታ የተወረሩ የከተማናና ገጠር መሬቶችእንዲመለሱና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል።

በቢሮ ኃላፊው አቶ አክመል አማካይነት የሴክተሩ የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ለመድረኩ እየቀረበ ይገኛል።

በ2017 በጀት አመት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የዞንና የልዩ ወረዳ መዋቅሮች የማበረታቻ ዋንጫና ሰርተፊኬት የ2018 በጀት አመት ዕቅድ የግብ ስምምነት እንደሚፈረም ለማወቅ ተችሏል።

በመድረኩ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ እና የክልሉ ብሔረሰቦች  ምክር  ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሴክተሩ ተዋንያን እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን

Image

Mon, 08 Sep 2025 08:40:16 +0000 Seble 184 at https://www.cerjustice.gov.et የገዢ ትርክትን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማስረጽና አንድነትን በማጠናከር የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን መሻገር እንደሚገባ ተገለጸ። https://www.cerjustice.gov.et/node/183 የገዢ ትርክትን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማስረጽና አንድነትን በማጠናከር የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን መሻገር እንደሚገባ ተገለጸ። Seble Sun, 09/07/2025 - 13:13

የገዢ ትርክትን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማስረጽና አንድነትን በማጠናከር የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን መሻገር እንደሚገባ ተገለጸ።

ሀላባ: ጳጉሜ/1/2017
ጳጉሜ-1 የጽናት ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ  በቁሊቶ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

ቀኑን በክላስተሩ የሚገኙ የክልል፣ የዞን፣ የቁሊቶ ከተማ አስተዳደርና የዌራ ወረዳ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም የከተማው ማህበረሰብ በጋራ አክብረውታል።

ቀኑን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን የጷጎሜ ቀናትን አከባበር አላማ አስረድተው፤ የዘንድሮውን የጷጎሜ ቀናት አከባበርን ልዩ የሚያደርገው ታላቁን የህዳሴ ግድብ አጠናቀን በምንመርቅበት ወቅት መሆኑ ነው ብለዋል።

በዕለቱ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢት የቀረበ ሲሆን "ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በቀረበው ሰነድ ኢትዮጵያ የአድዋ ድልን ጨምሮ ሀገር በማጽናት ረገድ የተጎናጸፈቻቸውን በርካታ የጦር ሜዳ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎች እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በስፋት ተዳስሷል።

የቀደመው ትውልድ ያጸናትን ሀገር አሁን ያለው ትውልድ ሀገሩን በመጠበቅ እና የልማት ስራዎችን በጽናት  በማከናወን ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው በፓናል ውይይቱ ተመላክቷል።

የገዢ ትርክትን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማስረጽና አንድነትን በማጠናከር የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን መሻገር ይገባል ተብሏል።

አቶ ኤርሴኖ ሀቡሬ - የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች በዚሁ መድረክ ተገኝተዋል።

የቀኑ አከባበር የብሄራዊ መዝሙር ተዘምሮ ተጠናቋል።

መ/ኮ

Image

Sun, 07 Sep 2025 10:13:05 +0000 Seble 183 at https://www.cerjustice.gov.et የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋና ፈጣን  የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዲከበር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፦ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ https://www.cerjustice.gov.et/node/182 የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋና ፈጣን  የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዲከበር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፦ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ Seble Fri, 09/05/2025 - 09:16

የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋና ፈጣን  የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዲከበር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፦ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ

(ነሐሴ 29/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ  የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር  ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ  የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋ፣ፈጣን እና ዘመናዊ የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት ለዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እና ነፃነት እንዲከበር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በፍትህ የተገልጋዩን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ ችግር ፈቺ  ቅንጅታዊ አሰራሮችን የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ዋና አፈ ጉበኤዋ አገልግሎትን በተለመደ አሰራር ሳይሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለህዝብ ተጠቃሚነት መስረት ይጠበቃል ብለዋል።

የፍትህ ተቋም ተገልጋይ የሚበዛበት ተቋም በመሆኑ በፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ የስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የግለጸኝነትና ተጠያቂነት ስርዓትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀጣይ ጥምረቱ ተግባራትን በዕቅድ በመምራት የግንኙነት አግባብን በማጠናከር  በፍትህ አገልግሎት የረካ ህብረተሰብን ለመፍጠር መትጋት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

የጥምረቱ ሰብሳቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ በበኩላቸው  የሚንፀባረቁ ችግሮችን በመለየት ለህዝብ የፍትህ ተደራሽነትን ለማድረስ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል።

በቀጣይ አሰራሩንና ህጉን  በመጠበቅ ጤናማ የሆነ የፍትህ ስርዓትን በመከተል ህዝቡ የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መትጋት ይገባል ብለዋል።

የምክክሩ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት የፍትህ ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በተጠያቂነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከህዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ አስፈጻሚ እና ፈጻሚ አካላት በተቀመጠው አሰራር መሰረት ህብረተሰቡ ትክክለኛ እና ቀልጠፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በባለቤትነት መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአስፈጻሚ እና ፈጻሚ አካላት የሚስተዋሉ የስነ ምግብር እና የክህሎት ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ይገባል ነው ያሉት።
የክልሉ መ/ኮ

Image

Fri, 05 Sep 2025 06:16:04 +0000 Seble 182 at https://www.cerjustice.gov.et የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2017 በጀት አመት የባለሙያዎችና የአቃቤ ህጎች የማትጊያና የእውቅና መርሃ ግብር አከናወነ! https://www.cerjustice.gov.et/node/181 የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2017 በጀት አመት የባለሙያዎችና የአቃቤ ህጎች የማትጊያና የእውቅና መርሃ ግብር አከናወነ!  Seble Wed, 08/20/2025 - 09:58

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2017 በጀት አመት የባለሙያዎችና የአቃቤ ህጎች የማትጊያና የእውቅና መርሃ ግብር አከናወነ!

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የሴክተሩን የ2017 አመታዊ አፈጻጸም መነሻ ያደረገ የባለሙያዎችና የማትጊያና የአቃቤ ህጎች የእውቅና መርሃ ግብር አከናውኗል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ ሬድዋን ኑሪ በ2017 መምሪያው በፈጸማቸው ተግባራትና ባስመዘገባቸው ውጤቶች ላይ የተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች አሻራቸውን ማኖራቸውን አስታውቀዋል።

የተሻለ ለፈጸሙ ባለሙያዎች እውቅና መስጠትና ማበረታታት የተቋምንና የግለሰቦችን የመፈጸም አቅም እንደሚያሳደግ ያስታወሱት አቶ ሬድዋን ከዚሁ መነሻ የሴክተሩ የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር መሰናዳቱን ገልጸዋል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞችና አቃቤ ህጎች በተለያዩ ዘርፎች ተከፍለው የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በዚሁ መሰረትም በአጠቃላይ ሰራተኞች፣ በሴቶች፣ በአቃቤ ህጎች እና ልዩ ተሸላሚ  በሚሉ ምድቦች የተቋሙ ሰራተኞች የማትጊያና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Image

Wed, 20 Aug 2025 06:58:49 +0000 Seble 181 at https://www.cerjustice.gov.et ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር ሐሳብ ላይ የጻፉት አራተኛውንና "የመደመር መንግሥት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ። https://www.cerjustice.gov.et/node/180 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር ሐሳብ ላይ የጻፉት አራተኛውንና "የመደመር መንግሥት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ። Seble Tue, 08/19/2025 - 11:31

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር ሐሳብ ላይ የጻፉት አራተኛውንና "የመደመር መንግሥት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።

Image

Tue, 19 Aug 2025 08:31:23 +0000 Seble 180 at https://www.cerjustice.gov.et ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ https://www.cerjustice.gov.et/node/179 ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ Seble Tue, 08/19/2025 - 11:28

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ለመላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች፣
ክልላችን ለተመሠረተበት ሁለተኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!አደረሰን !

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበት  ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት እነሆ ሁለት
ዓመት ሆነዉ።
እነዚህ ሁለት የትግልና የስኬት ዓመታት ፦በሁሉም መስኮች ተጨባጭ ዉጤቶች የተመዘገቡባቸዉ ፣በየምዕራፉ ካገጠሙ ፈተናዎች ትምህርት የተወሰደባቸዉ፣ የሕዝቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ የመጣባቸዉ፣ ሠላማዊ ፣ ጠንካራና ምሳሌ ሊሆን የሚችል ክልል ለመፍጠር የሚያስችሉ ምቹ መደላድሎች እዉን የሆኑባቸዉ፣
በአጠቃላይ ክልላዊ  ቁመናችን እያደገና እየደረጃ  ብሎም  በፈጠራና በፍጥነት መርህ  ታግዞ  'ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ! በማራመዱ ሂደት ክልሉ የበኩሉን እያበረከተ የተጓዘባቸዉ ናቸዉ ማለት ይቻላል።
_ ዉለዉ ያደሩ የመዋቅር ጥያቄዎች በክልል ምስረታዉ ማግስት ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል፣ የመዋቅር  ጥያቄዉ መመለስም ህዝቡ ትኩረቱን በልማትና በሠላም ግንባታ ላይ እንዲያደርግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
_አዎንታዊና ዘላቂ ሠላምን በህዝቦች ተሳትፎ እዉን ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ ፣ የህብረተሰቡን ሠላምና ደህነት  እዉን ከማድረግ ፣ ለልማትና ለአብሮነት አደናቃፊ  የሆኑ ችግሮችን ከማቃለል አኳያ  ዉጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል።የተረጋጋና ሠላማዊ ከባባዊ ሁኔታም ተፈጥሯል ፣

_ክልላዊ ፀጋዎችን እና አቅሞችን መሠረት ያደረጉ የልማት ንቅናቄዎችን በማጠናከር የምግብ ሉዓላዊነትን እዉን ለማድረግ እና ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር አጋዥ የሆኑ አበረታች ተግባራዊ  እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል፤አበረታች ዉጤቶችም ተመዝግበዋል።

_በከተሞችና በገጠር የመልካም አስተዳደር  ችግሮችን ለመፍታት ፣ የኑሮ ዉድነትን ለማቃለል  ጥረት ተደርጓል ።

_የየደረጃዉን አመራር የአስተሳሰብና የድርጊት ዉህደት፣ ትጋት፣ ሕዝባዊነትና ዉጤታማነት ለማሳደግ በተደረገዉ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል በአመራር ስርዓቱ ላይ እድገት እየታየ መጥቷል፤ የህዝቦችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሻሻል በፀና አቋም ላይ ተመስርቶ በተሠራዉ ሥራም ዉጤቶች ተገኝተዋል።
_ በብዙ ቢሊዬን ብር  የሚቆጠሩ ከቀድሞ ክልል የተሸጋገሩ  ያደሩ ዕዳዎችን መክፈል ተችሏል ፣
_ነባር  ፕሮጄክቶችን ለማጠናቀቅ  ጥረት ከማድረግ ባሻገር አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ጀምረናል፣ ለአብነትም በሰባቱም የክልል ማዕከላት የቢሮዎች ሕንፃዎችን እየገነባን እንገኛለን።

በአጠቃላይ  በፖለቲካው ፣ በኢኮኖሚው እና በማህበራዊ  ዘርፎች የተሠሩ ሥራዎች እና የተገኙ አበረታች  ዉጤቶች ለቀጣዩ ጉዟችን መደላድል  እና ሰንቅ ሆነዉ የሚያገለግሉ ፣ የህዝቦችን ተሳትፎ በማጠናከር  ለህዝቦች ተጠቃሚነት በታደሰ መንፈስ እንድንተጋ የሚያነሳሱ ናቸዉ። በመሆኑም  በቀጣይ  ጉድለቶችን እያረምን፣ ስኬቶችን እያፀናን፣ የህዝቦችን የመልካም  አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እንሠራለን ።

የተከበራችሁ መላዉ የክልላችን ሕዝቦች!

ያለፉት ሁለት ዓመታት ጉዞ በሚያስደንቅ የሕዝቦች ተሳትፎ የታጀበ ነበር፤ ይህ ሕዝባዊ ድጋፍ የየደረጃዉ አመራር ይበልጥ እንዲተጋ፣የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ደግሞ እንዲሳለጡ ጉልህ ሚና ተጫዉቷል።

የክልሉ መንግስት በሁሉም መስኮች ፈጣን መሻሻልና  ለዉጥ እንዲረጋገጥ በላቀ ትጋት ለመሥራት ያለዉን ቁርጠኝነት በዚህ አጋጣሚ  እያረጋገጥኩ  ፤ የክልሉ ሕዝቦች  ላደረጋችሁት  ሁለንተናዊ  ድጋፍ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ፣ ድጋፉ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል አደራ እላለሁ ።
አመሠግናለሁ !

ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image

Tue, 19 Aug 2025 08:28:46 +0000 Seble 179 at https://www.cerjustice.gov.et የሉሲ(ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት በመካከለኛው አውሮፓ በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት በአዲስ መልክ ያስተዋውቃሉ - ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ https://www.cerjustice.gov.et/node/178 የሉሲ(ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት በመካከለኛው አውሮፓ በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት በአዲስ መልክ ያስተዋውቃሉ - ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ Seble Fri, 08/15/2025 - 10:24

የሉሲ(ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት በመካከለኛው አውሮፓ በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት በአዲስ መልክ ያስተዋውቃሉ - ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ

ነሐሴ 9/2017)፦ የሉሲ(ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት በመካከለኛው አውሮፓ በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት በአዲስ መልክ እንደሚያስተዋውቁ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ወደ ቼክ ሪፐብሊክ ለሚሄደው የሉሲ (ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት አሸኛኘት አድርጓል።

በመርሀ ግብሩ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና በኢትዮጵያ የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚሮስላቭ ኮሴክ ተገኝተዋል።

ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ በዓለም ከምትታወቅበት መለያ አንዱ የሰው ዘር መገኛነቷ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንንም ገጽታ ለመገንባት እንዲሁም ለዓለም ለማስተዋወቅ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በዛሬው እለትም የሉሲ (ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት ወደ ቼክ ሪፐብሊክ እንደሚሄዱ አስታውቀዋል።

ቅሪተ አካላቱ በፕራግ ብሔራዊ ሙዝየም ለህዝብ እይታ እንደሚቀርቡም ነው የገለጹት።

ቅሪተ አካላቱ በቼክ ሪፐብሊክ በሚኖራቸው ቆይታ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ገልጠው እንደሚያሳዩ ጠቁመዋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት በአዲስ መልክ እንደሚያስተዋውቁ ሚኒስትሯ አመላክተዋል።

በተጓዳኝም የሁለትዮሽ የንግድ ፎረሞች እና ሌሎች ሁነቶች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።

የፕራግ ብሔራዊ ሙዝየም ዳይሬክተር ጀነራል ሚካኤል ሉኬሽ በበኩላቸው የቅሪተ አካላቱ በሙዝየሙ ለእይታ መቅረባቸው ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል።

ቅሪተ አካላቱ በታሪካዊ ቦታ ላይ ለእይታ እንደሚቀርቡ ጠቁመው ይህንን እውን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የሉሲ (ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካላት ለሰው ዘር አመጣጥ ምርምር ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ቅርሶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
#ኢዜአ

Image

Fri, 15 Aug 2025 07:24:29 +0000 Seble 178 at https://www.cerjustice.gov.et በመስቃንና ማረቆ በአካባቢው የተገኘው አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለፀ። https://www.cerjustice.gov.et/node/177 በመስቃንና ማረቆ በአካባቢው የተገኘው አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለፀ። Seble Fri, 08/15/2025 - 10:18

በመስቃንና ማረቆ በአካባቢው የተገኘው አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለፀ።

ነሀሴ 08/2017ዓ.ም ቢሮው በመስቃንና ማረቆ  አካባቢ እስካሁን ያለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የክልል ፣የዞንና ልዩ ወረዳው የፀጥታ መዋቅሮችና ኮማንድ ፖስት ጋር በቡታጅራ ከተማ ገምግሟል።

ባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ሰላምን የማፅናት ተግባራት  ቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተጠናክሮ መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምናፀጥታ ቢሮና የክልሉ ፍትህ ቢሮ   ከባለድርሻ አካላት ጋር በገመገመበት ወቅት ገልጿል።

የማዕከላዊ ኢትዮያጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እንደገለፁት  በአካባቢው የተገኘው አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ቀጠናው ሁከትና ብጥብጥ በማድረግ ትርፍ አምራች የሆነውን ማህበረሰብ ተመፅዋች ለማድረግ የጥፋት ዓላማ ያደረጉ እንቅስቃሴዎች በተሰሩ ጠንካራ ስራ  መቀልበስ መቻሉ አንስተዋል።

በተሰሩት ስራዎች ወንጀሎችና አጥፊዎች እርምጃ እንዲወሰድባቸው እየተደረገ መሆኑን  አብራርተዋል ።

የህዝብ አንድነትና መከባበር  ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ባህልና እሴቶቻችን በመጠቀም ሰላም የማፅናትን ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባ አመላክቷል።

የሰላም ዕጦትና ፀር የሆኑትን ግጭት ጥላቻንና መናናቅን የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅኖ በመገንዘብ  በፍቅርና በአብሮነት አሸናፊ በመሆን የአካባቢው ሰላም ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ሰላምን በማረጋገጥ ተረጂነትና ኃላቀርነትን የሚፀየፍ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባም አንስተዋል።

ኮማንድ ፖስቱ በተለያዩ ጊዜያት በተሰሩ ስራዎች ልምድ በማካበቱን  ጠቅሰው በአካባቢው ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ  አርአያ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች መኖራቸው እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ቡድንተኝነት፤ጎሰኝነትና ራስ ወዳድነት የሰላም ጠንቅ ናቸው ያሉት ኃላፊው አብሮነትና አንድነት በሚያሰርፅ መልኩ በተለያዩ መድረኮች ሰፋፊ የግንዛቤ ስራዎች መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አክመል አህመድ በአካባቢው የተፈጠረው ችግር  በህግ አግባብ በመፍታት ዘላቃ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ማህበረሰብ ያገኘው አንፃራዊ ሰላም በተገቢዉ መጠበቅ ያስፈልጋል ያሉት ኃላው ግጭት ፈጣሪዎችንና በማህበራዊ ሚዲያ ግጭት የሚፈጥሩ አካላት መከታተል እንደሚገባ አንስተዋል።

በመድረኩ  በኮማንድ ፖስት በቀረበው ሪፖርት የእስካሁኑ አፈፃፀሙ የተመዘገቡ ውጤቶችና በሂደቱ የታዩ ጉድለቶችን በመለየት በዝርዝር ተገምግመዋል።

በአካባቢው የተከሰተው የፀጥታ ችግር ወደመደበኛ ሰላም ለማምጣት መላው ህብረተሰብ ወጣቶች የአካባቢ አስተዳዳር አካላት ከፀጥታ ሀይል ጎን ሆነው ለተሰሩ ስራዎች ቢርው ምስጋና ሰጥቷል።

በሂደቱ ፈተናዎችን በማሻገር በእውቀት በጥበቡ ቁርጠኝነት በመመራቱ ከነበሩበት ውስብስብና አስቸጋሪ ሁኔታ መሻገር የተቻለ መሆኑን ተነስቷል።

በአጠቃላይ በተሰጡ  ግቦች  መሰረት እስካሁን  ያልተከናወኑ ተግባራት ተለይተው በተቀመጠለት  የጊዜ ሰሌዳ  መሰረት እንዲጠናቀቅ  አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Image

Fri, 15 Aug 2025 07:18:57 +0000 Seble 177 at https://www.cerjustice.gov.et የማዕከላዊ ኢትዮያጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በመስቃንና ማረቆ አካባቢ እስካሁን ያለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በቡታጅራ ከተማ እየገመገመ ነው https://www.cerjustice.gov.et/node/176 የማዕከላዊ ኢትዮያጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በመስቃንና ማረቆ አካባቢ እስካሁን ያለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በቡታጅራ ከተማ እየገመገመ ነው Seble Fri, 08/15/2025 - 10:10

የማዕከላዊ ኢትዮያጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  በመስቃንና ማረቆ አካባቢ እስካሁን ያለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በቡታጅራ ከተማ እየገመገመ ነው

ነሀሴ 8/2017 የማዕከላዊ ኢትዮያጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  በመስቃንና ማረቆ  አካባቢ   እስካሁን ያለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቡታጅራ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮያጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊና የክልሉ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ካሳ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አመራሮች ተገኝተዋል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ

Image

Fri, 15 Aug 2025 07:10:32 +0000 Seble 176 at https://www.cerjustice.gov.et የቱሪዝም ዘርፍ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ https://www.cerjustice.gov.et/node/175 የቱሪዝም ዘርፍ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ Seble Thu, 08/14/2025 - 11:46

የቱሪዝም ዘርፍ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ

(ነሐሴ 8/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የስልጢ_ቡታጅራ ጂኦ ፓርክ ክልላዊ ማስጀመሪያ መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ  አቶ ሳሙኤል መንገሻ እንደተናገሩት እንደ ክልል በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ከዘርፉ ማግኘት ያለበትን ጥቅም ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።

በክልሉ 11 የቱሪስት መስህቦችን ለማልማት ፕሮጀከት ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን በመግለጽ መስህቦች ለምቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የጂኦ ፓርክ  የምክክር መድረክ ለቀጣይ ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ የሚረዳ እንደሆነም ተናግረዋል።

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ በበኩላቸው የቱሪዝም ዘርፍን ማሳደግ ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ የአካባቢውን ገፅታ ለመገንባትም የሚጫወተው ሚና  ከፍተኛ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ከመድረኩ የስልጢ_ቡታጅራ ጂኦ ፓርክ ዙሪያ ለሚሰራው ተግባር የጋራ ግንዛቤ ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩም ከቱሪዝም ሚኒስቴር የመጡ  ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ

Image

Thu, 14 Aug 2025 08:46:59 +0000 Seble 175 at https://www.cerjustice.gov.et