Seble
Sat, 07/12/2025 - 15:27
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አስጀምሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምጸሀይ ጳውሎስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በማስጀመሪያው የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
በተጨማሪም በአበሽጌ ወረዳ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ፣ የአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና የጽዱ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ተጀምሯል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
Image
