የሰብዓዊ መብቶች ድርጊት መርሀ ግብር ማስተባበሪያ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነትየማስተባበሪያ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
በክልል ደረጃ የድርጊት መርሀ ግብሩን አፈጻጸም በክልላዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጡት አቅጣጫዎች መሰረት ይከታተላል።
በመርሀ ግብሩ እንዲከናወኑ የተቀመጡ ተግባራት፤ ፈጻሚ አካላት ተብለው በተለዩት የክልል ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ መካተታቸውን ይከታተላል፤
በየተቋማቱ ውስጥ ከተደራጁት የድርጊት መርሀ ግብሩ ተወካዮች/Focal Person/ ጋር በቅርበት ይሰራል፤
ተቋማት በየሩብ ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በወቅቱ አሰባስበው መላካቸውን ይከታተላል፤
በየሩብ ዓመቱ ክልል አቀፍ የድርጊት መርሀ ግብሩን አፈጻጸም ሪፖርት በማጠናቀር ለክልላዊ አስተባበሪ ኮሚቴ እና ለፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ድርጊት መርሀግብር ፅ/ቤት ያቀርባል፤
የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መመርመር፣ እንዲመረመሩ ማድረግ፤
ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በፌደራል ደረጃ የወጣው የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ-ግብር በክልሉ ውስጥ ያለውን ተፈፃሚነት መከታተል፤ በክልል-አቀፍ ደረጃ ተሳታፊ የሚሆኑትን ወገኖች እንቅስቃሴ ማስተባበር፤ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ማቅረብ፤
ሀገሪቱ ያፀደቀቻቸው ወይም የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች በክልሉ ውስጥ ያላቸውን ተፈጻሚነት መከታተል፤ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ሲቀርብለት ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ረገድ መተባበር፣ ማገዝ፤
የህግ አስከባሪ አካላት የሃይል አጠቃቀምና ተጠያቂነት ሥርዓት በተመለከተና ሌሎች ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የተያያዙ የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጅ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተባብሮ መስራት፤
ሌሎች በዘርፉ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ማከናወን፤