የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነትየዓቃብያነ ሕግ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ምደባና ደረጃ እድገት ስራዎችን ይሰራል፤ የውሳኔ ሀሳብ ለዐቃቤ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ በማቅረብ ያፀድቃል፤
የዐቃብያነ ህግ የዲስፕሊን ጉዳዮችን በማጣራት የውሳኔ ሀሳብ ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዐቃብያነ ህግ አስተዳር ዋና ጉባኤ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፤ ውሳኔው ይፈጽማል፤
የዐቃብያነ ህግ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና የመሳሰሉ ጉዳዩችን ያካተተ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዋና ጉባኤ ተተችቶ ለመስተዳድር ም/ቤት እንዲቀርብ ያደርጋል፤
በዋናው ጉበኤ የሚሰጡትን የተለያዩ ስራዎች ጨምሮ የዓቃብያነ ህጉን መረጃ በአግባቡ የመያዝ እና አስተዳደራዊ አገልግልቶችን ይሰጣል፡፡
ዐቃበያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ የሚወስናቸውን እና የሚሰጣቸውን ውሳኔዎች እና ትዕዛዞች አፈጻፀም መከታተልና ሲፈለግ ለጉባኤው ያቃርባል፣
በዐቃብያነ ህግ የሚቀርቡ የዲስፕሊን ጉዳዮችን በማደራጀት ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ የሚፈቱበትን ሁኔታዎች ማማከር፣
የዐቃቢያነ ህግ መብት ጥያቄዎችን በመቀበል ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዋናው ጉባኤ የሚወሰንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
የክልሉን ዐቃብያነ ህግ ማስተዳደር ጋር ተያይዞ በቢሮ ኃላፊ የሚሰጡ ማንኛውንም ህጋዊ ትዕዛዝ መፈጸምና ማማከር፡፡