በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪ
የማስተባበሪያወ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመተባበር ክልላዊ በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ግብረ-ሃይልን ዕቅድ የማዘጋጀትና ዕቅዱን ለፈጻሚ ተቋማት እንዲደርስ ማድረግ፤
- በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል የሚሰሩ በክልል እንዲሁም በዞን ደረጃ የተቋቋመዉን ግብረ ሃይል ማስተባበር፣ መደገፍ፣ መከታተል፤
- ክልላዊ በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል የማስተማሪያ ማንዋል ማዘጋጀትና ለክልል ፈጻሚ ተቋማት፣ ለዞንና፣ ለከተማ አስተዳደር፣ ለወረዳዎች እንዲደርሳቸው ማድረግ፤
- ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር ተጎጂዎች ስላላቸው መብት፣ የተጎጂዎችን ደህንነት ለመጠበቅ፣ ለመታደግና ወደ አገራቸው ለመመለስ ስለሚያስችሉ በሥራ ላይ ስላሉ የሕግ ወይም ሌላ መንገዶች፣ ተጎጂዎች መረጃ እና ድጋፍ ሊያገኙ ስለሚችሉባቸው ድርጅቶች፣ ተቋማትና የሕግ አስከባሪ አካላት መረጃን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጥ፤
- ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር ተጎጂዎች በተለይም ሴቶችና ሕጻናት ለእነዚህ ወንጀሎች እንዲዳረጉ የሚገፋፉ ምክንያቶችን ለማዳከም የሚያስችሉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራት፤
- አገሪቱ በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ዙሪያ የፈረመቻቸውና ያፀደቀቻቸውን እንዲሁም የህግ አካል ያደረገቻቸውን ህጎች፣ ደንቦች ፕሮቶኮሎች በክልሉ ያላቸውን ተፈጻሚነት መከታተልና ማስተግበር፤
- በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውጤታማ የቅንጅትና የትብብር አሰራሮችን መዘርጋት፤
- በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን አስመልክቶ ተጠርጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን፣ ቦታዎችን እና የወንጀል ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች አስመልክቶ ክትትል እንዲደረግባቸው ከልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር መረጃ መለዋወጥ፤ አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ግብረ ኃይል እና አባል ተቋማት የተከናወኑ ተግባራትን በማጠቃለል፣ በማደራጀት እና አፈጻጸሙን በመገምገም ሪፖርቱን ለክልሉ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል መከላከል ምክር ቤት እና ለፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንዲደርስ ማድረግ፤
- ሌሎች በዘርፉ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ማከናወን፤