የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነትበደንብ ቁጥር 84/2003 ለስነምግባር መከታተያ ክፍል የተሰጠው ስልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ፤
በተቋሙ ውስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፣
በፀረ-ሙስና፣ በሥራ ዲስፒሊን፣ በሙያ ሥነ-ምግባር፣ በሕዝብ አገልጋይነትና ኃላፊነት ስሜት ላይ የተለያዩ ትምህርትና ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስናን መሸከም የማይችል ሠራተኛ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፣
የፀረ-ሙስና ፖሊሲዎችና ሕጎች መከበራቸዉን መከታተል፤ ስለ አፈጻጸማቸዉ የቢሮ ኃላፊ ማማከር፣
የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር እንዲጋለጥ፣ እንዲመረመርና በአጥፊዎች ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ፣
የሙስና ወንጀል የሚያጋልጡ ሰራተኞች ላይ የቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የበላይ አመራሩን ማማከር፣
የተቋሙን የሙስና መከላከያ ስትራቴጅ ተግባራዊነት ይከታተላል፣
የሥነ-ምግባር ጥሠቶችን ወይም ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት ለበላይ አመራር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣
የተቋሙ ሠራተኞች ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር ወይም ስልጠና እንዲሁም ማንኛዉም የግዥ አገልግሎት ከሕግና ደንብ ውጭ ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ለቢሮ ኃላፊ ማቅረብ፣
ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በጥናት የመለየትና የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ፣
በስር መዋቅር የሥነ-ምግባር ኦፊሰሮች የተሟሉ መሆኑን በማረጋገጥ መደገፍና ሥራዉን መምራት፣
በተቋሙ በየደረጃዉ በሚሰጡ አገልግልቶች ላይ ከተገልጋዮችና ሕብረተሰቡ ጥቆማ የሚሰጥበትን ስርዓት መዘርጋት፣ ነጻ የስልክ ጥሪን እና ሌሎች አማራጮችን መፍጠር