Skip to main content
                        የሰብዓዊ መብቶች ድርጊት መርሀ ግብር ማስተባበሪያ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት

                                                                 ማስተባበሪያ ዋናዋናተግባርናኃላፊነት

  •      በክልል ደረጃ የድርጊት መርሀ ግብሩን አፈጻጸም በክልላዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጡት አቅጣጫዎች መሰረት ይከታተላል።
  •      በመርሀ ግብሩ እንዲከናወኑ የተቀመጡ ተግባራት፤ ፈጻሚ አካላት ተብለው በተለዩት የክልል ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ መካተታቸውን ይከታተላል፤
  •      በየተቋማቱ ውስጥ ከተደራጁት የድርጊት መርሀ ግብሩ ተወካዮች/Focal Person/ ጋር በቅርበት ይሰራል፤
  •      ተቋማት በየሩብ ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በወቅቱ አሰባስበው መላካቸውን ይከታተላል፤ 
  •      በየሩብ ዓመቱ ክልል አቀፍ የድርጊት መርሀ ግብሩን አፈጻጸም ሪፖርት በማጠናቀር ለክልላዊ አስተባበሪ ኮሚቴ እና ለፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ድርጊት መርሀግብር ፅ/ቤት ያቀርባል፤ 
  •      የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መመርመር፣ እንዲመረመሩ ማድረግ፤
  •     ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በፌደራል ደረጃ የወጣው የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ-ግብር በክልሉ ውስጥ ያለውን ተፈፃሚነት መከታተል፤ በክልል-አቀፍ ደረጃ ተሳታፊ የሚሆኑትን ወገኖች እንቅስቃሴ ማስተባበር፤ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ማቅረብ፤
  •    ሀገሪቱ ያፀደቀቻቸው ወይም የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች በክልሉ ውስጥ ያላቸውን ተፈጻሚነት መከታተል፤ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ሲቀርብለት ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ረገድ መተባበር፣ ማገዝ፤
  •    የህግ አስከባሪ አካላት የሃይል አጠቃቀምና ተጠያቂነት ሥርዓት በተመለከተና ሌሎች ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የተያያዙ የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጅ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተባብሮ መስራት፤
  •     ሌሎች በዘርፉ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ማከናወን፤