የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- የዓቃብያነ ሕግ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ምደባና ደረጃ እድገት ስራዎችን ይሰራል፤ የውሳኔ ሀሳብ ለዐቃቤ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ በማቅረብ ያፀድቃል፤
- የዐቃብያነ ህግ የዲስፕሊን ጉዳዮችን በማጣራት የውሳኔ ሀሳብ ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዐቃብያነ ህግ አስተዳር ዋና ጉባኤ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፤ ውሳኔው ይፈጽማል፤
- የዐቃብያነ ህግ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና የመሳሰሉ ጉዳዩችን ያካተተ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዋና ጉባኤ ተተችቶ ለመስተዳድር ም/ቤት እንዲቀርብ ያደርጋል፤
- በዋናው ጉበኤ የሚሰጡትን የተለያዩ ስራዎች ጨምሮ የዓቃብያነ ህጉን መረጃ በአግባቡ የመያዝ እና አስተዳደራዊ አገልግልቶችን ይሰጣል፡፡
- ዐቃበያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ የሚወስናቸውን እና የሚሰጣቸውን ውሳኔዎች እና ትዕዛዞች አፈጻፀም መከታተልና ሲፈለግ ለጉባኤው ያቃርባል፣
- በዐቃብያነ ህግ የሚቀርቡ የዲስፕሊን ጉዳዮችን በማደራጀት ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ የሚፈቱበትን ሁኔታዎች ማማከር፣
- የዐቃቢያነ ህግ መብት ጥያቄዎችን በመቀበል ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዋናው ጉባኤ የሚወሰንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
- የክልሉን ዐቃብያነ ህግ ማስተዳደር ጋር ተያይዞ በቢሮ ኃላፊ የሚሰጡ ማንኛውንም ህጋዊ ትዕዛዝ መፈጸምና ማማከር፡፡