የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክክሬት
የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- ከፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር ለክልሉ ፍትህ ቢሮ በውክልና የተሰጡ የወንጀል ጉዳዮችን፣በክልል ዓቃቤ ህግ ስልጣን ስር በሚወድቁ ከሙስና ነክ ወንጀልና የታክስ ህጎችን በመጣስ ከሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ዉጭ ያሉ የወንጀል ድረጊቶችን ይከታተላል፣ ተገቢውን ህጋዊ ዉሳኔ ይሰጣል፡፡
- ከባድ እና ዉስብስብ በሆኑ የወንጀል ድርጊቶች የወንጀል ምርመራ ከፖሊስ ጋር አብሮ ያጣራል ወይም እንዲጣራ ያደርጋል፤ ምርመራውን በበላይነት ይመራል፡፡
- በዳይሬክቶሬቱ ስልጣን ስር የተሰጡ ወንጀሎች ስለመፈጸማቸው በቂ ጥርጣሬ ሲኖሩ ወይም ጥቆማ በቀረበ ጊዜ ተገቢው ምርመራ ተጣርቶና በበቂ ማስረጃ ተደግፎ እንዲቀርብ ማድረግ፤
- በሀሰተኛ ምስክሮች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ መወሰን፣ ዉጤቱን መከታተል፣
- በተጠርጣሪዎች የሚቀርብ የዋስትና መብት ይከበርልኝ፣ በዋሶች የሚቀርብ ዋስትና ይነሳልኝ ወይም በዋስትና የተያዘ ንብረት ይለቀቅልኝ የሚል አቤቱታ ለፍ/ቤት ቀርቦ መልስ እንዲያቀርብ ሲታዘዝ መልስ በማቅረብ ክርክር ማድረግ፤
- በወንጀል ከተጠረጠሩ ሰዎች በምርመራ ምክንያት በኤግዚቪትነት የተያዙ ንብረቶች አፋጣኝ ውሳኔ የሚያገኙበትን የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤ አፈጻጸማቸውን መከታተል፤ መገምገም እና አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን መስጠት፤
- ከዞን/ልዩ ወረዳ የሚቀርቡ የይግባኝ ቅሬታዎችን መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጣል፤ ይግባኝ ለመጠየቅ ብቁ በሆኑ ጉዳዮች በየትኛዉም ደረጃ ስልጣን ባላቸዉ ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ይጠይቃል ወይም መልስ እንዲሰጥ በተጠየቀባቸዉ ጉዳዮች መልስ ይሰጣል፣
- በፖሊስ ጣቢያና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎችን የመጎበኘት፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሰረት መፈጸሙን የማረጋገጥ፣ሕገ ወጥ ተግባር ተፈፅሞ እንደሆነ እንዲታረም የማድረግ፡ ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ የመዉሰድ ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
- በፍርድ ቤት ውሳኔ ያረፈባቸውን ንብረቶች በፍርዱ መሰረት ማስፈጸም፤ ፍትሐብሔራዊ ክርክር የሚያስነሱ ሆነው ከተገኙ ክርክር እንዲደረግባቸው ለፍትሐብሔር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማሳወቅና ሙሉ መረጃ መስጠት፤
- ወደ ዳይሬክቶሬቱ የሚመጡ የክስ ይነሳልኝ ወይም ይሻሻልልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፤ መመርመርና በህግ አግባብ ውሳኔ መስጠት፤
- ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ለመከላከልና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ማድረግና አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት፤
- በየደረጃው በሚቀርቡ ይግባኞች ላይ ክርክር ማድረግ፣ ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ማቅረብ፤ ለይግባኝና ሰበር አቤቱታ ምላሽ መስጠት፤
- ውስብስብ በሆኑ የወንጀል መዛግብት እና ከስር ዐቃብያነ ህግ በሚቀርቡ መሪ ትዕዛዝ ጥያቄዎች ላይ በጋራ ወይም በፓናል መወሰን፤
- ከፖሊስ ጋር በሚደረገው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ተቀናጅቶ መስራት፤
- የሰበር አቤቱታዎችን በማዘጋጀት ስልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት ያቀርባል ወይም ተጠሪ በሆነባቸዉ የሰበር አቤቱታዎች ተገቢዉን ምላሽ ይሰጣል፤ ይከራከራል፣
- እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛዉም የክልሉ አከባቢ በሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮች ከፖሊስ ጋር ሆኖ ምርመራ ያጣራል፡፡ ቀጥታ ክስም ሊያቀርብ ይችላል፡፡
- የዞኖችንና የልዩ ወረዳዎችን ስራ ይከታተላል፤ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል ሌሎች ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ተግባራት ያከናዉናል፡፡