የሴቶችና ሕጻጻት ልዩ የምርመራና ክስ ክትትል ዳይሬክቶሬት
የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
የዚህ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት የሚመነጨው እድሜና ጾታ መሰረት ተደርገው የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤
ፆታና እድሜ መሰረት ያደረጉ ከባድ እና ውስብስብ የወንጀል ድርጊቶች የወንጀል ምርመራ ከፖሊስ ጋር አብሮ ያጣራል ወይም እንዲጣራ ያደርጋል፤ ምርመራውን በበላይነት ይመራል፡፡
- በዳይሬክቶሬቱ ስልጣን ስር የተሰጡ ወንጀሎች ስለመፈጸማቸው በቂ ጥርጣሬ ሲኖሩ ወይም ጥቆማ በቀረበ ጊዜ ተገቢው ምርመራ ተጣርቶና በበቂ ማስረጃ ተደግፎ እንዲቀርብ ማድረግ፤
- ክስ በቀረበባቸው ጉዳዮች ላይ ምስክሮች የሚያስረዱትን ተገንዝቦ፣ የክርክር ፍሬ ነገሮችን ከቀጠሮው በፊት አጥንቶና ተዘጋጅቶ በመቅረብ መከራከር፤
- በሀሰተኛ ምስክሮች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ መወሰን፣ ዉጤቱን መከታተል፣
- በተጠርጣሪዎች የሚቀርብ የዋስትና መብት ይከበርልኝ፣ በዋሶች የሚቀርብ ዋስትና ይነሳልኝ ወይም በዋስትና የተያዘ ንብረት ይለቀቅልኝ የሚል አቤቱታ ለፍ/ቤት ቀርቦ መልስ እንዲያቀርብ ሲታዘዝ መልስ በማቅረብ ክርክር ማድረግ፤
- በወንጀል ከተጠረጠሩ ሰዎች በምርመራ ምክንያት በኤግዚቪትነት የተያዙ ንብረቶች አፋጣኝ ውሳኔ የሚያገኙበትን የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤ አፈጻጸማቸውን መከታተል፤ መገምገም እና አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን መስጠት፤
- ከዞን/ልዩ ወረዳ የሚቀርቡ የይግባኝ ቅሬታዎችን መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጣል፤ይግባኝ ለመጠየቅ ብቁ በሆኑ ጉዳዮች በየትኛዉም ደረጃ ስልጣን ባላቸዉ ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ይጠይቃል ወይም መልስ እንዲሰጥ በተጠየቀባቸዉ ጉዳዮች መልስ ይሰጣል፣
- የሰበር አቤቱታዎችን በማዘጋጀት ስልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት ያቀርባል ወይም ተጠሪ በሆነባቸዉ የሰበር አቤቱታዎች ተገቢዉን ምላሽ ይሰጣል፤ ይከራከራል፣
- እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛዉም የክልሉ አከባቢ በሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮች ከፖሊስ ጋር ሆኖ ምርመራ ያጣራል፡፡ ቀጥታ ክስም ሊያቀርብ ይችላል፡፡
- በፖሊስ ጣቢያና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎችን የመጎበኘት፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሰረት መፈጸሙን የማረጋገጥ፣ሕገ ወጥ ተግባር ተፈፅሞ እንደሆነ እንዲታረም የማድረግ፡ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ የመዉሰድ ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
- በፍርድ ቤት ውሳኔ ያረፈባቸውን ንብረቶች በፍርዱ መሰረት ማስፈጸም፤ ፍትሐብሔራዊ ክርክር የሚያስነሱ ሆነው ከተገኙ ክርክር እንዲደረግባቸው ለፍትሐብሔር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማሳወቅና ሙሉ መረጃ መስጠት፤
- ወደ ዳይሬክቶሬቱ የሚመጡ የክስ ይነሳልኝ ወይም ይሻሻልልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፤ መመርመርና በህግ አግባብ ውሳኔ መስጠት፤
- ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ለመከላከልና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ማድረግና አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት፤
- በየደረጃው በሚቀርቡ ይግባኞች ላይ ክርክር ማድረግ፣ ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ማቅረብ፤ ለይግባኝና ሰበር አቤቱታ ምላሽ መስጠት፤
- ውስብስብ በሆኑ የወንጀል መዛግብት እና ከስር ዐቃብያነ ህግ በሚቀርቡ መሪ ትዕዛዝ ጥያቄዎች ላይ በጋራ ወይም በፓናል መወሰን፤
- ከፖሊስ ጋር በሚደረገው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ተቀናጅቶ መስራት፤
- የዞኖችንና የልዩ ወረዳዎችን ስራ ይከታተላል፤ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል
- እንደአስፈላግነቱ በመዝገቦች ላይ የክስ ዉክልና ይሰጣል፤
- በሴቶችና ሕጻናት የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ከረጂ ድርጅቶች/ዩኒሴፍ/ ጋር በቅንጅት ይሰራል. ግንዛቤ ይፈጥራል፤
- ሌሎች ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ተግባራት ያከናዉናል፡፡