Seble
Fri, 02/21/2025 - 10:10
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት እናከስር መዋቅር አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት ፤ የ1ኛ ግማሽ ዓመት በዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሄደ።
ጥር 9/2017 ዓ.ም
የማዕ/ኢት/ክልል/ መንግስት ፍትህ ቢሮ የ 2017 ዓመት 1ኛ ግማሽ ዓመት በዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እናከዞን/ ከልዩ ወረዳ ፍትህ መምሪያ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የልማት ዕቅድ አስተባባሪዎችጋር በሀላባ ከተማ የግምገማ መድረክ አካሄዷል።
በተቀናጃ የፍትህ አገልግሎት ውጤት ለማስመዝገብ እየሰራ እንደሆነ የገለጸው ቢሮችግሮች ነቅሶ በመለየት እና እርምት በመውስድ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራና በቅንጅት ለመሠራት የገለጸ ሲሆን ቢሮው የዜጎችን የፍትህ ፍላጎት ለማርካት የተሰጠውን ኃላፊነት እና ተግባር በትጋትና በተጠየቂነትእንዲሁም ከተጠሪ ተቋማት እና ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት በጋራ በመስራት መሆን እንደሚገባ ገልጿል።
በዕለቱ የፍትህ ቢሮልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬትተወካይ አቶጌታሁን ፍቅሩ ዕቅድ ሪፖርቱን አቅረበው: ከተጠሪ ተቋማት፤ ከስር መዋቀር ኃላፊዎች አስተያየት ማብራራያ ጥያቄ ተነስቶ ምላሽ ተስጥቶባቸው እናበቀሪ 6ወርዙሪያ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
ለዘገባው: የቢሮው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን
Image
