Skip to main content
                             የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶረት

                                                         የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት

  •      በቢሮው ማቋቋሚያ አዋጅ 03/2016 አንቀጽ 5/7/ከሀ-በ የተጠቀሱ ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ስራ ላይ ያውላል፡፡
  •     ከክልሉ መንግሥት ተቋማት የሚመነጩ የሕግ ሀሳቦችን እንዲሁም በሌሎች አካላት ተዘጋጅተው የቀረቡ ረቂቅ ህጎችን ከሕገ-መንግሥቱም ሆነ ከክልሉና ከፌደራል መንግሥቱ ሕግጋት ጋር የተጣጣሙ ስለመሆናቸው በማረጋገጥ ጥራታቸውን የጠበቁ ረቂቅ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ማዘጋጀት እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት ሙያዊ አስተያየት ማቅረብ፤
  •     የክልሉ መንግሥት ሕጎች ተግባራዊ መደረጋቸውንና አተገባበራቸውም ወጥነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ስራቸውን በሕግ መሰረት ማከናወናቸውን በቅርበት መከታተል፤
  •     በስራ ላይ ያሉትን የክልሉን ሕጎች በየጊዜው በማጥናት ወይም በሌሎች እንዲጠኑ በማድረግና የማሻሻያ የውሳኔ ሃሳብ በማዘጋጀት ለክልሉ መንግሥት ማቅረብ፣ ሲፈቀድም ለማሻሻያዎቹ የሚያስፈልጉትን ረቂቆች በማዘጋጀት ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቦ ማስጸደቅ፤
  •     በክልሉ ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸውን የክልልና የፌደራል መንግሥት ሕግጋት ማሰባሰብ፣ ማጠቃለል፣ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በህግጋቶች ላይ የሚታዩ የህግ ግድፈቶች ሲያጋጥሙ እንዲታረሙ ለሚመለከታቸው አካላት መላክ፤
  •     ከውል ረቂቅ ምርመራ፣ ከውል ዝግጅትና ከሌሎች ፍትሐብሔራዊ ባህሪ ካላቸው የህግ ጉዳዮች ውጭ ያሉ የሕግ ጉዳዮችን በተመለከተ የክልሉን መንግሥት ተቋማት ማማከር፤
  •    ዐቃብያነ-ሕግ ስለ ስራቸው ያላቸውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት በተከታታይና በየደረጃው ለማሳደግ ይቻላቸው ዘንድ ተገቢውን የአቅም ግንባታ እንዲያገኙ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን ማስተባበር እንደአስፈላጊነቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ስልጠና መስጠት፣ እንዲሰጥ ማድረግ እንዲሁም የስልጠና ጥሪ ማስተላለፍ፤
  •    የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ለክልሉ መንግስት ባለስልጣናት፣ ለሌሎች ተሿሚዎች፣ የህዝብ ተመራጮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም ለግሉ ዘርፍ ተሳታፊዎች እንዳስፈላጊነቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ የንቃተ-ሕግ መርሃ-ግብሮችን ማዘጋጀት፣ ስልጠና መስጠት ወይም እንዲሰጥ ማድረግ፤
  •     ከህግ ምክር፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ስራዎች ጋር በተያያዘ ከህግ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ማከናወን፤
  •    የሕግ ምክር ፣የሕግ ማርቀቅ፣የህግ ማረምን፣ የሕግ ጥናትን የሕጎች ማሰባሰብና ማጠቃለል፣የሕግ ስልጠናን (በማዘጋጀት፣ በመሳተፍና በማስተባበር)፣ የሕግ ትምህርትን ፣በቤተ-መፅሃፍትና ድክመንቴሽን ፣ የህግ የትርጉም ስራ እና  ማሻሻያ ስራዎች ይሰራል፡፡ 
  •     ሌሎች ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ተግባራት ያከናዉናል፡፡