Skip to main content
                                       የቢሮው ሥልጣንና ተግባር

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከዚህ ቀደም በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የወጡና በደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ ታውጀው ስራ ላይ ያሉ ህጎች ተገቢው ማሻሸያ ተደርጎላቸው በክልሉ ነጋሪት ጋዜጣ እስከሚታወጁ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል በማለት በክልሉ ነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 198/2015 እና የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 199/2015 በተደነገገው መሰረት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 177/2011 ለፍትህ ቢሮ የተሰጡ ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት፤ 

  • በሕግ ጉዳዮች የክልል መንግስት ዋና አማካሪ እና ተወካይ ሆኖ መስራት፣
  • በፌደራል መንግስት ተዘጋጅቶ የጸደቀውን የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ማስተባበር፣ መከታተልና ማረጋገጥ፣
  • የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት፣ መተንተንና ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋትና ማስፈጸም፣
  • በፌዴራልና በክልሉ ሕገ-መንግስታት እና በሌሎች ሕጎች የተደነገጉ የግልና የቡድን መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ፣
  • በክልሉ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር በሚወድቁ በማናቸውም የሙስና እና የታክስ ህጎችን በመጣስሚፈፀሙወንጀል ጉዳዮች እንዲሁም ከባድና ውስብስብ በሆኑ ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች የወንጀል ምርመራ ከፖሊስ ጋር አብሮ ማጣራት፣ ምርመራውን በበላይነት መምራት፣
  • በሕዝብ ጥቅም መነሻ ወይም በወንጀል የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልፅ ሲታወቅ የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ ወይም የተቋረጠው የወንጀል ምርመራ እንዲቀጥል ማድረግ፤ማናቸውም የወንጀል ምርመራዎች በሕግ መሰረት መከናወናቸውን ማረጋገጥ፤ አስፈላጊውን ህጋዊ ትእዛዝ ለሚመለከተው አካል መስጠት፣
  • ምርመራቸው በፖሊስ በተጀመረባቸው መካከለኛ፣ ቀላል እና በግል አቤቱታ በሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ በአግባቡ ስለመከናወኑ በቅርበት ክትትል ማድረግ፤በተጀመረ የወንጀል ምርመራ አስመልክቶ ፖሊስ ለዓቃቤ ህግ ማሳወቁን ማረጋገጥ፣
  • በወንጀል መዝገብ ላይ የተሰጠ የዓቃቤ ሕግና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ለሚመለከተው ፖሊስ ማሳወቅ፣ የወንጀል ምርመራ መዝገቦችን አስመልክቶ በየደረጃው ባሉ ዓቃቤያነ ሕግ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ በፖሊስ የሚቀርቡ አቤቱታ ተቀብሎ ውሳኔ መስጠት፤ 
  • የተጠናቀቁ የምርመራ መዝገቦችን ከሕግና ከማስረጃ አንፃር መርምሮ በሕግ የተቀመጡ መመዘኛዎች ሲሟሉ የአያስከስስም ወይም የተዘግቷል ውሳኔ መስጠት፤ 
  • የጥፋተኝነት ድርድር ይወስናል፣ ድርድር ያደርጋል፣ አማራጭ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ መወሰን፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፤ 
  • መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዩች ክስ ይመሰረታል፣ ይከራከራል፣ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው  ክስ ማንሳት፣ የተነሳ ክስ እንዲቀጥል ማድረግ፣
  • የወንጀል ድርጊት ጠቋሚዎችና ምስክሮች በህግ መሰረት ጥበቃና ከለላ እንዲያገኙ ማድረግ፣
  • በማረፊያ ቤትና  በማረሚያቤት ቁጥጥር ሥር ያሉ ተጠሪጣሪዎችንና ታራሚዎችን መጎብኘት፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሰረት መፈጸሙን ማረጋገጥ፣ ሕገ ወጥ ተግባር ተፈፅሞ እንደሆነ እንዲታረም ማድረግና ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ መውሰድ ወይም እንዲወሰድ ማድረግ፤
  • በዕርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶች በእርቅ የሚጠናቀቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
  • ፍቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጧቸው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች መፈፀማቸውና መከበራቸውን መከታተል፣ ሳይፈፀሙ ከቀሩ ወይም አፈፃፀማማቸው ሕግን ያልተከተለ ከሆነ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለሰጠው ፍ/ቤት በማመልከት የዕርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤
  • በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ማደራጀት ወይም መደራጀታቸውን ማረጋገጥ፣
  • የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በኩል እንዲቀርብ ማድረግ፣ አፈፃፀሙን መከታተል፣
  • በክልል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የሕዝብ እና የክልል መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ መከራከር፣ ማስከበር፣ እንዲከበሩ ማድረግ፣ የሚከበሩበትን ሂደት መከታተል፣ መቆጣጠር፣
  • ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የውል ዝግጅት እና ድርድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ማድረግ፣ የሕዝብና የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ውል እና የመግባቢያ ሰነዶች ዝግጅትና ድርድር ማድረግ ወይም የሚመለከታቸውን አካላት ማማከር፣ 
  • የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶችን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ መመስረት፤ በከሰሱበት ወይም በተከሰሱበት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ክርክር ማድረግ፤ በተጀመረ ክርክር ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ መከራከር፣ ወይም በክርክር አመራር ላይ ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ መስጠት፣ በሕግ መሠረት ለተሰጡ ውሳኔዎች ፍርድን ማስፈጸም፤
  • በክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና በግል ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች መካከል የሚከሰቱ የፍትሐብሔር ክርክሮች በድርድር እንዲያልቁ ጥረት ማድረግ፣ ድርድሩ ካልተሳካ ጉዳዩን ስልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት አቅርቦ መከራከር፣
  • የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሳኔ ሀሳብ መስጠት፣ በውሳኔው መሰረት መፈፀሙን ማረጋገጥ፤
  • የተመዘበረ የመንግስት ገንዘብ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ማስመለስ፣ የሙስና ወንጀል ውጤት የሆኑት እና በፍርድ ሂደት ላይ ያሉ ንብረቶችን ማስተዳደር፤ እንዲወረስ ውሳኔ የተሰጠባቸውን ንብረቶች ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማስተላለፍ፣
  • የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ መከራከር፤
  • የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዩች እንዲካሱ መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐብሔር ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ ማቅረብ ወይም መደራደር፤
  • በክልል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች የሕግ ረቂቅ ዝግጅት ስራ  መስራት፤ የመንግስት አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ህግ ከፌዴራልና ከክልሉ ሕገ መንግስትና ከሌሎች ሕጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ለሚመለከታቸው ክፍሎችም አስተያየት ማቅረብ፤
  • በክልሉ በስራ ላይ ባሉ ህጎች ጥናት በማድረግ ሕጎች እንዲሻሻሉ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣ ሲደገፍም ለተባሉት ማሻሻያዎች ረቂቆችን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ፣
  • ሕጐችን የማሰባሰብ፣ የማጠቃለልና የኮዲፊኬሽን ሥራ ይሰራል፤ የክልሉን ህጎች በባለአደራነት መያዝ፣ ማሰራጨት፤
  • ዐቃቤያነ ሕግ ስለ ስራቸው ያላቸውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት  በተከታታይ እና በየደረጃው ለማሳደግ ትምህርት እና ሥልጠና መስጠት ወይም እንዲሰጣቸው ማድረግ፤ 
  • የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ለማዳበር ለክልሉ ህብረተሰብ በተለያዩ ዜደዎች የንቃተ ህግ ትምህርት መስጠት፣ 
  • በክልሉ ፍርድ ቤቶች ለሚከራከሩ ጠበቆች ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ስራቸውን መቆጣጠር፣ የጠበቆችን ዲሲፕሊን ጉዳዮች አይቶ መወሰን፤ በህግ መሰረት መሰረዝ፣
  • በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያውያን ማህበራትን መመዝገብ፣ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት፣ ስራቸውን መቆጣጠር፣ ማረጋገጥ እና በሕግ መሰረት መሰረዝ፣
  • አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ሰነዶችን መመዝገብ፣ ማረጋገጥ፣  መሻር፣ መሰረዝ፣
  • ነፃ የሕግ ድጋፍ አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን መቅረጽ፣ አፈፃፀሙን መከታተል፣ በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን ማስተባበር፣
  • ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀግብር መነሻ በማድረግ ክልላዊ ሰብአዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ማዘጋጀት፣ አፈፃፀሙን መከታተል፤ በክልል ደረጃ የሚመለከታቸውን አካላት ማስተባበር፣ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ማቅረብ፣ 
  • የዐቃቤ ሕግ የውሳኔ አሰጣጥ እና የፍቅደ ሥልጣን አጠቃቀም ወጥነትን ለማረጋገጥ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፀደቀ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን ማረጋገጥ፣    
  • በዓቃቤያነ ሕግ የሚሰጡ ውሳኔዎች በሕግ መሰረት መከናወናቸውን የሚያረጋግጥ  የኢንስፔክሽን ክፍል ማደራጀት፣ ጉድለቶችን በጥናት አስደግፎ መለየት፤ በግኝቱ መሠረትም እንዲታረሙ ማድረግ፣ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ መውሰድ ወይም እንዲወሰድ ማድረግ እና መልካም ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት፣
  • የክልሉን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ሥራዎች በበላይነት መምራት፣ መከታተል፣ ማስተባበር፤ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ የሚያገኙበትን ስርዓት መዘርጋት፤
  • በሕግ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ወይም ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡