Skip to main content
                        የታክስ ነክ  ወንጀሎች ዳይሬክቶረት 

                                                       የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት

  •    በክልል መንግስት የወጡትን የታክስ ህጎችን በመጣስ የሚፈፀሙትን ወንጀሎች ወይም በፌዴራል መንግስት ወጥተዉ በክልሉ በቀጥታ ወይም በዉክልና የተሰጡ ጉዳዮችን ይከሳል፤ያስወስናል፡፡
  •    በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወይም በዞኖችና በልዩ ወረዳዎች ከሚደራጀዉ የታክስ ህጎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ጋር ሆኖ ከጥቆማ ጀምሮ ምርመራ የሚያጣራ  የዓቃቢያነ ህግ ቡድን               ያደራጃል፤ አሰራራቸዉን ይከታተላል፡፡
  •    የታክስ ህጎችን በመጣስ የሚፈፀሙትን ወንጀሎች ከመርመሪ ፖሊሶች ጋር በጋራ ይመረምራል፣ ያጣራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤ይከታተላል፣ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል፤ ይከራከራል፡፡ 
  •    የታክስ ወንጀል ጥቆማ ወይም አቤቱታ ወይም መዝገብ በመቀበል መረጃ ያደራጃል፣ምላሽ ይሰጣል፣ጉዳይን ለሚከታተል አካል የጥቆማ ወይም የመዝገብ መለያ ቁጥር ይሰጣል፤
  •    በተጠርጣሪዎች የሚቀርብ የዋስትና መብት ይከበርልኝ፣ በዋሶች የሚቀርብ ዋስትና ይነሳልኝ ወይም በዋስትና የተያዘ ንብረት ይለቀቅልኝ የሚል አቤቱታ ለፍ/ቤት ቀርቦ መልስ እንዲያቀርብ ሲታዘዝ  መልስ             በማቅረብ ክርክር ማድረግ፤
  •    በታክስ ስወራና ምዝበራ የተጠረጠሩ ሰዎችን ሃብት እንዲጣራ ማድረግ፤ የታገዱና በኤግዚቪትነት የተያዙ ንብረቶችና ገንዘቦች አያያዝና አመላለስን በተመለከተ ውጤታማና ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓቶችን           መዘርጋት፤ አፈጻጸሙን መከታተል፤ መገምገም እና አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን መስጠት፤ እንዲወረሱ ወይም እንዲመለሱ በሚል የፍርድ ቤት ውሳኔ ያረፈባቸውን ንብረቶች ለመንግስት ገቢ ማስደረግ፤              ፍትሐብሔራዊ ክርክር የሚያስነሱ ሆነው ከተገኙ ክርክር እንዲደረግባቸው ለፍትሐብሔር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማሳወቅና ሙሉ መረጃ መስጠት፤
  •    ክስ በቀረበባቸው ጉዳዮች ላይ ምስክሮች የሚያስረዱትን ተገንዝቦ፣ የክርክር ፍሬ ነገሮችን ከቀጠሮው በፊት አጥንቶና ተዘጋጅቶ በመቅረብ መከራከር፤ 
  •    የህዝብና የመንግሥት ጥቅምን በማይጐዳ /በማይጻረር/ መንገድ በታክስ ስወራና ምዝበራ ወንጀል ከተጠርጣሪዎች /ከተከሳሾች/ ጋር  ድርድር ያደርጋል፤
  •    ምርመራ ከመርመሪ ፖሊሶች ጋር በጋራ ይመረምራል፣ ያጣራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤ይከታተላል፣
  •     የዞኖችንና የልዩ ወረዳዎችን ስራ ይከታተላል፤ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል 
  •    ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል፤ ይከራከራል፣ ያስወስናል፡፡
  •    የይግባኝ እና ሰበር ጉዳዮች ይከታተላል፣
  •    የፌዴራል ጉዳዮች ከፍትህ ሚኒስቴር ዉክልና ሲሰጠዉ ይከሳል፣ያስወስናል
  •    ተከሳሾችና ምስክሮች እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
  •    የተመዘበረ ሀብት ያስመልሳል፡፡
  •     በመዝገቦች ላይ ዉሳኔ ይሰጣል፣
  •    እንደአስፈላግነቱ በመዝገቦች ላይ የክስ ዉክልና ይሰጣል
  •     ለሥራ ግብ ስኬት አስፈላጊ ከሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሠነድ ይፈራረማል፣
  •    ሌሎች ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ተግባራት ያከናዉናል፡፡