የሙስና ነክ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት
የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- በክልሉ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቁ የሙስና ወንጀሎችን ምርመራ ይመራል፣ ይከሳል፤ ያስወስናል፡፡
- ለዞንና ልዩ ወረዳዎች የተሰጡ የመመርመርን የመክሰስ ስልጣን በአግባቡ እየተከናወነ ስለመሆኑ በቅርበት ይከታተላል፡፡
- በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወይም በዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ከሚደራጀዉ የሙስና ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ጋር ሆኖ ከጥቆማ ጀምሮ ምርመራ የሚያጣራ የዓቃቢያነ ህግ ቡድን ያደራጃል፣ አሰራራቸውን ይከታተላል፡፡
- የሚቀርቡ ቅሬታዎችን/አቤቱታዎችን መቀበል፤ ለሚመለከታቸው በመላክ እንዲጣራ ማድረግ፤ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በመገምገም መወሰን፣
- በተጠርጣሪዎች የሚቀርብ የዋስትና መብት ይከበርልኝ፣ በዋሶች የሚቀርብ ዋስትና ይነሳልኝ ወይም በዋስትና የተያዘ ንብረት ይለቀቅልኝ የሚል አቤቱታ ለፍ/ቤት ቀርቦ መልስ እንዲያቀርብ ሲታዘዝ መልስ በማቅረብ ክርክር ማድረግ፤
- በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎችን ሃብት እንዲጣራ ማድረግ፤ የታገዱና በኤግዚቪትነት የተያዙ ንብረቶችና ገንዘቦች አያያዝና አመላለስን በተመለከተ ውጤታማና ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት፤ አፈጻጸሙን መከታተል፤ መገምገም እና አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን መስጠት፤ እንዲወረሱ ወይም እንዲመለሱ በሚል የፍርድ ቤት ውሳኔ ያረፈባቸውን ንብረቶች ለመንግስት ገቢ ማስደረግ፤ ፍትሐብሔራዊ ክርክር የሚያስነሱ ሆነው ከተገኙ ክርክር እንዲደረግባቸው ለፍትሐብሔር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማሳወቅና ሙሉ መረጃ መስጠት፤
- የይግባኝ ክርክሩ ታይቶ እስኪወሰን የመንግስትን ጥቅም የሚጎዳ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ካለ ሳይፈፀም ታግዶ እንዲቆይ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አቤቱታ እንዲቀርብ ማድረግ፣ አቤቱታው በወቅቱ መቅረቡንና ትዕዛዙ/ዕግዱ መሰጠቱን መከታተል፣
- ለሙስና ወንጀልና ከባድ የስነ-ምግባር ጥሰት ጠቋሚዎችና ምስክሮች የአካልና የስራ ዋስትና ጥበቃ የሚሰጥበትን ሁኔታ ከበላይ አመራር ጋር በመመካከር ማመቻቸት፣ መከታተል፣ መተግበር እና የተወሰደ የበቀል እርምጃ ካለ በህግ አግባብ ማገድ፣ ማጣራትና አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በስውር የሙስና ወንጀል መረጃ የሚሰበሰብባቸውን አካላት ከቢሮ ኃላፊና ዘርፉን ከሚመራው ኃላፊ ጋር ሆኖ መለየት፤ መምራት፤ መከታተል፣
- ወደምስክር የሚዞሩ ተጠርጣሪዎችን ቃል መገምገም፣ መወሰን፣ በበላይ አመራር ሲወሰን ቃል እንዲሰጡ ማድረግ፣
- ልዩ ጉዳይ ሲያጋጥምእና ሁኔታው አስፈላጊ ሲያደርገው አንድን የምርመራ ወይም የንብረት ጥናት ስራዎች በተለየ ሁኔታ ወይም በቡድን ማከናወን፤ አፈፃፀሙን መከታተል፣
- በሀሰተኛ ምስክሮች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ መወሰን፣ ዉጤቱን መከታተል፣
- የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን የስልክ፣ የፖስታና ሌሎች ሚስጥራዊ ግንኙነት እንዲጠለፍ የዉሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፣ ውሳኔውን መተግበር፣ አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በሙስና የተጠረጠሩ ባለስልጣናትን እና ያለመከሰስ መብት ያላቸዉ ተጠርጣሪዎችን የወንጀል ተሳትፎ መገምገም፣ መወሰን፣ በበላይ አመራር ሲወሰን ቃል እንዲሰጡ ማድረግ፣
- ክስ በቀረበባቸው ጉዳዮች ላይ ምስክሮች የሚያስረዱትን ተገንዝቦ፣ የክርክር ፍሬ ነገሮችን ከቀጠሮው በፊት አጥንቶና ተዘጋጅቶ በመቅረብ መከራከር፤
- ወደ ዳይሬክቶሬቱ የሚመጡ የክስ ይነሳልኝ ወይም ይሻሻልልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፤ መመርመር፤ የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ አመራር አቅርቦ ውሳኔ ሲሰጥ ተግባራዊ ማድረግ፤
- የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶች ማድረግና አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት፤
- በየደረጃው በሚቀርቡ ይግባኞች ላይ ክርክር ማድረግ፣ ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ማቅረብ፤ ለይግባኝና ሰበር አቤቱታ ምላሽ መስጠት፤
- ውስብስብ በሆኑ የወንጀል መዛግብት እና ከስር ዐቃብያነ ህግ በሚቀርቡ የመሪ ትዕዛዝ ጥያቄዎች ላይ በጋራ ወይም በፓናል መወሰን፤
- የሙስና ወንጀል ጥቆማ ወይም አቤቱታ ወይም መዝገብ በመቀበል መረጃ ያደራጃል፣ምላሽ ይሰጣል፣ጉዳይን ለሚከታተል አካል የጥቆማ ወይም የመዝገብ መለያ ቁጥር ይሰጣል፤
- ምርመራ ከመርመሪ ፖሊሶች ጋር በጋራ ይመረምራል፣ ያጣራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤ይከታተላል፣
- ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል፤ ይከራከራል፣ ያስወስናል፡፡
- የይግባኝ እና ሰበር ጉዳዮች ይከታተላል፣
- በሙስና ወንጀል ተጠሪጣሪዎችን ወይም ተከሳሾችን ሀብትና ንብረት ያጠናል፤ በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንድታገድ ያደርጋል፡፡
- የፌዴራል ጉዳዮች ከፍትህ ሚኒስቴር ዉክልና ሲሰጠዉ ይመረመራል፣ ይከሳል፣ያስወስናል
- የተመዘበረ ሀብትና ንብረት ያስመልሳል፡፡
- የህዝብና የመንግሥት ጥቅምን በማይጐዳ /በማይጻረር/ መንገድ በማናቸውም የሙስና ወንጀል ከተጠርጣሪዎች /ከተከሳሾች/ ጋር ድርድር ያደርጋል፤
- ተከሳሾችና ምስክሮች እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
- በመዝገቦች ላይ ዉሳኔ ይሰጣል፣
- እንደአስፈላግነቱ በመዝገቦች ላይ የክስ ዉክልና ይሰጣል
- የዞኖችንና የልዩ ወረዳዎችን ስራ ይከታተላል፤ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል
- ለጠቋሚዎችና ምስክሮች ከለላ ይሰጣል፣
- ሌሎች ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ተግባራት ያከናዉናል፡፡