የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
በደንብ ቁጥር 84/2003 ለስነምግባር መከታተያ ክፍል የተሰጠው ስልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ፤
- በተቋሙ ውስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፣
- በፀረ-ሙስና፣ በሥራ ዲስፒሊን፣ በሙያ ሥነ-ምግባር፣ በሕዝብ አገልጋይነትና ኃላፊነት ስሜት ላይ የተለያዩ ትምህርትና ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስናን መሸከም የማይችል ሠራተኛ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፣
- የፀረ-ሙስና ፖሊሲዎችና ሕጎች መከበራቸዉን መከታተል፤ ስለ አፈጻጸማቸዉ የቢሮ ኃላፊ ማማከር፣
- የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር እንዲጋለጥ፣ እንዲመረመርና በአጥፊዎች ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ፣
- የሙስና ወንጀል የሚያጋልጡ ሰራተኞች ላይ የቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የበላይ አመራሩን ማማከር፣
- የተቋሙን የሙስና መከላከያ ስትራቴጅ ተግባራዊነት ይከታተላል፣
- የሥነ-ምግባር ጥሠቶችን ወይም ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት ለበላይ አመራር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣
- የተቋሙ ሠራተኞች ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር ወይም ስልጠና እንዲሁም ማንኛዉም የግዥ አገልግሎት ከሕግና ደንብ ውጭ ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ለቢሮ ኃላፊ ማቅረብ፣
- ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በጥናት የመለየትና የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ፣
- በስር መዋቅር የሥነ-ምግባር ኦፊሰሮች የተሟሉ መሆኑን በማረጋገጥ መደገፍና ሥራዉን መምራት፣
- በተቋሙ በየደረጃዉ በሚሰጡ አገልግልቶች ላይ ከተገልጋዮችና ሕብረተሰቡ ጥቆማ የሚሰጥበትን ስርዓት መዘርጋት፣ ነጻ የስልክ ጥሪን እና ሌሎች አማራጮችን መፍጠር