አቶ አክመል አህመዲን ሶማ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
የክልሉ ፍትህ ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 3/2016 ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባራት መካከል ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓትን ማክበርና በማስከበር የህግ የበላይነትንና ማረጋገጥ፣ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ማስጠበቅ ዋና ዋና ተግባራት ሲሆኑ ተቋሙ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊ፣ ተደራሽ፣ እና ውጤታማ የፍትሕ አገልግሎት በመስጠት የሕዝብ አመኔታ ማግኘት የተቋሙ ተልዕኮ ነው፡፡
ይሁንና የፍትህ ሥርዓቱ በተቋም አደረጃጀቱና አሠራሩ ኃላ ቀር፣ በብሮክራሲ እና በብልሹ አሠራር የተተበተበና በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ያሉበት ስለመሆኑ በሀገራዊ ጥናት እና በተሰበሰቡ በክልላዊ መረጃዎች ተረጋግጧል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ3 ዓመት የሚቆይ የፍትህ ትራንስፎረሜሽን ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ መተግበር ከጀመረ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ በዚህ ፍኖተ ካርታ የተዘረዘሩ አስሩአምዶች በተያዘላቸው ጊዜ ዉስጥ ወደ ተግባር በመቀየር የፍትሕ አገልግሎቱን ማዘመን፣ ሳቢና ታማኝነት የተቸረው ማድረግ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡
በመሆኑም በክልላችን ብሎም በሀገራችን የተጀመረው የልማትና የዕድገት ጉዞ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና መሸጋገር ይቻል ዘንድ የፍትህ ሴክተሩን ጥቁር ካባ ያለበሱ፣ስሙን ያበላሹና የተገልጋዩን አመኔታ የሸረሸሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ብልሹ አሠራሮችን በህዝብና በባለድርሻ አካላት በላቀ ተሣትፎ ችግሩን መቅረፍ ይጠበቅብናል፡፡ በየደረጃው የሚገኝ የፍትህ ሴክተር አመራር፣ ባለሙያ እና ድጋፍ ሠጪ ሠራተኞች በጋራ ተቋማችን ለማዘመን፣ ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ እንድንችል ከወረስነው ጎታታ አሠራርና አስተሳሰብ በፍጥነት ተመንጭቀን በመውጣት ወደ ለውጥ ጎዳና እንድንገባ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡
“ፍትህ ለሁሉም”