የህግ ኦዲትና እንስፔክሽን እና ቅሬታ ማስተናገጃ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
በወንጀልና በፍትሐብሔር መዝገብ ላይ የተሰጡ የማቋረጥ ወይም የመዝጋት ውሳኔዎችን ሕጋዊነትና አግባብነት ምክንያት ቅሬታው ለቢሮ ኃላፊ ሲቀርብ መመርመርና የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣
በክልል ማዕከል ጀምሮ እስከ ስር መዋቅር ወደ ፍ/ቤት የቀረቡ ክሶች በሕግ አግባብ የቀረቡ መሆኑን በታቀደ ወይም ድንገተኛ የሕግ ኦዲት ሥራ ማረጋገጥና ዉጤቱን ለዋና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቅርቦ በሚያግባባ ጉዳይ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
ጥቆማን ወይም የበላይ አመራር ትዕዛዝን መነሻ በማድረግ ማንኛዉንም የዓቃቤ ሕግ ውሳኔዎችን ሕጋዊነት በኦዲትና ኢንስፔክሽን ያጣራል፣
ዐቃቢያነ ሕግ በተቋሙ የወጡ መመሪያዎችንና የተዘረጉ አሰራሮችን ጠብቀዉ እየሰሩ መሆኑን ያረጋግጣል፣
በኦዲት ግኝቶች ላይ ተመስርቶ ግብረ መልስና ማስተካከያ እንዲደረግ ለኦዲት ተደራጊዉ የሥራ ክፍል መላክና የበላይ አመራሩ እንዲያውቀው ማድረግ፣አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
የኦዲት ግኝትን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል አጣርቶ ለበላይ አመራር የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣
በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚቀርቡ ማንኛዉንም ቅሬታዎች ተቀብሎ በሚመለከተዉ ክፍል እንዲጣሩ ወይም እንዲፈቱ ይልካል፣
ለዳይሬክቶሬቱ የተላኩ አቤቱታዎች/ቅሬታዎች በወቅቱ ምላሽ ስለማግኘታቸዉ መከታተል፣ ተገልጋዮች በዜጎች ቻርተር መሰረት አገልግሎት እያገኙ መሆን አለመሆኑን መከታተልና በተቋሙ ያለውን የተገልጋዮችን የእርካታን ደረጃ በጥናት ይለያል፣
የሥራ ክፍሎች በተቀመጠው የተቋሙ አሰራርና ሕግ መሰረት አገልግሎት ስለመስጠታቸው ማረጋገጥ እና የቅሬታ ምንጮችን በጥናት በመለየት የመፍትሔ ሀሳብ ያቀርባል፣