Skip to main content
                              የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት

በደንብ ቁጥር 84/2003 ለስነምግባር መከታተያ ክፍል የተሰጠው ስልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ፤

  •   በተቋሙ ውስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፣ 
  •   በፀረ-ሙስና፣ በሥራ ዲስፒሊን፣ በሙያ ሥነ-ምግባር፣ በሕዝብ አገልጋይነትና ኃላፊነት ስሜት ላይ የተለያዩ ትምህርትና ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስናን መሸከም የማይችል ሠራተኛ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፣
  •   የፀረ-ሙስና ፖሊሲዎችና ሕጎች መከበራቸዉን መከታተል፤ ስለ አፈጻጸማቸዉ የቢሮ ኃላፊ ማማከር፣ 
  •   የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር እንዲጋለጥ፣ እንዲመረመርና በአጥፊዎች ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ፣
  •   የሙስና ወንጀል የሚያጋልጡ ሰራተኞች ላይ የቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የበላይ አመራሩን ማማከር፣
  •   የተቋሙን የሙስና መከላከያ ስትራቴጅ ተግባራዊነት ይከታተላል፣
  •   የሥነ-ምግባር ጥሠቶችን ወይም ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት ለበላይ አመራር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣
  •   የተቋሙ ሠራተኞች ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር ወይም ስልጠና እንዲሁም ማንኛዉም የግዥ አገልግሎት ከሕግና ደንብ ውጭ ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ለቢሮ ኃላፊ ማቅረብ፣
  •   ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በጥናት የመለየትና የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ፣
  •   በስር መዋቅር የሥነ-ምግባር ኦፊሰሮች  የተሟሉ መሆኑን በማረጋገጥ መደገፍና ሥራዉን መምራት፣ 
  •   በተቋሙ በየደረጃዉ በሚሰጡ አገልግልቶች ላይ ከተገልጋዮችና ሕብረተሰቡ ጥቆማ የሚሰጥበትን ስርዓት መዘርጋት፣ ነጻ የስልክ ጥሪን እና ሌሎች አማራጮችን መፍጠር