የፍትሀብሄር ጉዳዮች ዳይሬክቶረት ተግባርና ኃላፊነት
የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 6/6/ከ ሀ-ሸ የተሰጡትን ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ስራ ላይ ያዉላል፡፡
- ከዞን እና ከአከባቢ ማስተባበሪያና ልዩ ወረዳ የሚመጡ ፍትሀብሄር ነክ ጥያቄዎችን እንደአስፈላጊነቱ መርምሮ አስፈላጊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
- በዞን በልዩ ወረዳ ደረጃ ወደ ታች በመውረድ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣሉ፣
- የምድብና ተዘዋዋሪ ችሎቶችን ክትትል ያደርጋል፡፡
- በፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎችን መርምሮ እንደአስፈላግነቱ ይግባኝ ወይም ሰበር ይጠይቃል፡፡በፍርድ ቤት በመገኘት ክርክር ያደርጋል፡፡
- ከሙስና እና ታክስ ወንጀሎች ጋር ተያይዞ በግለሰቦች ወይም በድርጅቶች የተመዘበሩ የመንግስት ሀብቶችን በተመለከተ ከየስራ ክፍሉ ጋር በመቀናጀት የፍትሀብሄር ክስ በመመስረት የማስመለስና የሚወረሱ ንብረቶችንም ያስወርሳል፡፡በህግ አግባብ የማስተዳደርና ለመንግስት በተገቢዉ ሁኔታ ገቢ ስለመሆናቸዉ ያረጋግጣል፡፡