Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ብሄራዊ ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀመሩ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ለተማሪዎቹ መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
.......................................//.........................................

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና በምግብ እራስን ለመቻል የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የ2017 የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እና የገጠር ኮሪደር የማስጀመር መርሐ ግብር ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና በምግብ እራስን ለመቻል የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለው ኢተገማች የአየር ንብረት ለውጥ የደኖች መመናመን እና የዓፈር ለምነት መቀነስ፣ የተባይና የበሽታ ክስተት መስፋፋት እያስከተለ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 
.......................................//.........................................

በ2017 በጀት አመት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተተገበሩ የነበሩ ስራዎች በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆናችንን ያመላክታል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 29ኛ መደበኛ ስብሰባ  ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት በ2017 በጀት አመት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተተገበሩ የነበሩ ስራዎች በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆናችንን ያመላክታል ብለዋል።

የበጀት አመቱ ከመግባቱ በፊት ለእቅድ ዝግጅት የተሰጠው ትኩረት አሁን በየደረጃው ለተመዘገበው ውጤት በምክንያትነት ተጠቃሽ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 
.......................................//.........................................

በ2018 ለመተግበር የታቀዱ ስራዎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ሊሆን ይገባል -  ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ሰሞኑን በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ መክሯል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እንደገለጹት በ2018 ለመተግበር የታቀዱ ስራዎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ እቅድ ብልሹ አሰራርን መከላከል፣አገልግሎት አሰጣጥን ማፋጠን ፣በቴክኖሎጂ እና በአሰራር ለላቀ ስኬት መትጋት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። 
.......................................//.........................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) እና የክልሉ የካቢኔ አባላት በሆሳዕና ከተማ  እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደት  ምልከታ አደረጉ

በክልሉ በሆሳዕና ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኙ የክልል ተቋማት የቢሮ ግንባታ ሂደት ርዕሰ መስተዳድሩ  እና በእርሳቸው የተመራ ልኡክ ምልከታ አድርገዋል።

የክልሉ መንግስት ከጀመራቸው አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ የተቋማት የቢሮ ህንጻ ግንባታ ተጠቃሽ ነው። 
........................................//........................................
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ563 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ ይለማል

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017/18 የመኸር ወቅት በተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ ከ563 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው።

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ በመኸር ወቅት ከሚለማው መሬት ከ54 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።

በአዝዕርት ሰብሎች 421 ሺህ 430 ሄክታር መሬት ለማልማትና 12 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመዋል።

Image
#የሳምንቱ #አበይት #ዜናዎቻችን....