Seble
Mon, 07/14/2025 - 10:58
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የ2017 ዞናዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሶዶ ወረዳ ጢያ ከተማ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው።
(ሆሳዕና፣ሐምሌ 06/2017)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩርና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ዞናዊ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም በሶዶ ወረዳ ጢያ ከተማ አስጀምረዋል።በዕለቱ ለምግብነት የሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬዎች በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።በዘንድሮው ዓመት በዞኑ ከሀያ አምስት ሚሊየን ችግኝ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በማሳተፍ የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው ፍራፍሬና አትክልቶች እንደሚተከሉ ተጠቅሷል።በመረሃ ግብሩ የዞኑ፣የወረዳውና የከተማ አስተዳደር አመራሮችና ነዋሪዎች አሻራቸውን ማኖራቸውን ከዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
Image
