የክልሉ ግብርና ቢሮ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ እና የግብርና ግብአቶችን በአግባቡ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለፀ።
(ሆሳዕና፦ሀምሌ 7/2017)፣ የክልሉ ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግብርናን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ልክነሽ ስርገማ እንዳሉት የአርሶአደሩን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ በግብርና ቢሮ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ነው ብለዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ እና የግብርና ግብአቶችን በአግባቡ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉን በግምገማው አንስተው ገበያ ተኮር የአመራረት ዘዴን በመከተል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገው ርብርብ ተጫባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል።
በሌማት ትሩፋት አርሶአደሩ ማሳቸውን በአግባቡ በመጠቀም የተለያዩ የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንሰሳት ተዋጽኦ ውጤቶችን እንዲጠቀሙ በማድረግ በኑሮአቸው የሚታዩ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ነው ወ/ሮ ልክነሽ የገለፁት።
ምርጥ ዘር፣ የእንስሳት ምርት ፣ የሰብል ምርት፣ የቡናና ቅመማ ቅመሞችን ለአርሶአደሩ በማቅረብ እንዲሁም ተጠቃሚነታቸውን እንዲያድግ የተደረገበት አግባብ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በመስኖ አጠቃቀም ህብረተሰቡ ከተለመደ አሰራር ተላቆ በመደበኛም ይሁን በበጋ መስኖ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል ብለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተጫባጭ ለውጦች እንዲመጣ የተደረገበት አግባብ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል።
በህብረት ስራ ልማት ተግባርም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማጠናከር የተሰሩ ስራ አበረታች ቢሆንም በቀጣይ የበለጠ ስራ ይጠይቃል ነው ያሉት።
በከተማ ግብርና በተሰራው ቅንጅታዊ ሰራ አመርቂ ውጤት መምጣቱን በመግለፅ በተፋሰስ ስራም ያሉ ተግባራት በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለው ከቆዳና ሌጦ የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት በልዩ ትኩረት መስራት ያስፈልጋል ነው የተባለው።
በአረንጓዴ አሻራ ተግባርም በርካታ ለምግብነት የሚሆኑ ፍራፍሬ በመትከል የተገኘው ውጤትም አበራታች እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ ልክነሽ ባህር ዛፍን በማስወገድ በሌላ ሰብል ምርት ለመተካት የተጀመረው ርብርብ መጠናከር ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል።
በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቢሮው የተሰሩ ስራዎችና ኢኒሼቲቮች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለው የጤፍ ምርታማነትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በግብርና ሴክተር ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የተፈጠረበት አግባብ በሌሎች ተቋማትም ልለመድ የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ከክልሉ ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለተነሱ ጥያቄዎች የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር እና የማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምንጭ የክልሉ መ/ኮ
