አመራር አካዳሚው በጥናትና ምርምር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራቱን የክልሉ ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።
(ሆሳዕና፦ሀምሌ 8/2017) ቋሚ ኮሚቴው የክልሉ አመራር አካዳሚ 2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ እንዳሉት በአካዳሚው በጥናትና ምርምር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል።
አካዳሚው ለተለያዩ አስፈጻሚዎችና ፈጻሚዎች የአቅም ግንባታ እየሰጠ ያለበት አግባብ የሚያበረታታ ነው ብለው በጥናትና ምርምር ዘርፍ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆንም ጥናቱ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።
አካዳሚው እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ክፍተቶችን በመለየት እየሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጨባጭ ለወጥ አምጥቶ የህዝብ ተጠቃሚነት እስከሚረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በአካዳሚው ስልጠና ከተሰጠ በኃላ የመጣውን ለውጥ በሚገባ የመለየት ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለው ስልጠና ለሚያስፈልጋቸው ተቋማት ፍላጎት የመለየት እና ውጤታማነቱ ላይ ሊሰራ ይገባል።
የሚሰጡ ስልጠናና ስርፀት ችግር ፈቺ እንዲሆን ጊዜ ተወስዶና በቂ በጀት ተመድቦለት ሊሰራ ይገባል ብለው ሰልጣኞቹ ከሚሰሩት ሙያ ጋር ተዛማጅነት ያለ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አቶ ግዛቸው ተናግረዋል።
በስልጠና ፋይዳ ደሳሳ በማድረግ የመጣውን ለውጥ በሚገባ በመገምገም የእርካታ ደረጃ መለየት ያስፈልጋል ብለው በቀጣይ ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች ተዘርግቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በተመሳሳይ የክልሉ ምክር ቤት የፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ገቢዎች ቢሮ የ2017 አፈጻጸምን የገመገመ ሲሆኑ ከቋሚ ኮሚቴቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ከተቋማቱ ቢሮ ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ
