Skip to main content

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እያከናወነ ያለው ስራዎች አበረታች መሆኑን የክልሉ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ገለጸ
=====

ሀምሌ 9/2017) የምክር ቤቱ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።

በተመሳሳይ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና ሴቶችና ህፃናት ቢሮ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በቋሚ ኮሚቴዎች ተገምግሟል።

የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እንደገለፁት ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተግባራትን ለመፈጸም የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል።

የፍርድ ቤቶችን ውጤታማነትና ቅልጥፍና በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እና መዘገብ የመጠራት ስራ በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

የመዛግብት መጨናነቅን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች አበራታች ቢሆን የበለጠ በመስራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማጎልበት ያስፈልጋል ሲሉ ወ/ ሮ መሰረት ተናግረዋል።

የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ እና ተከሳሽ እና ምስክሮች በመጥፋቱ ምክንያት በሚቋረጡ ክሶች ዙሪያ የተለየ ግብ ተጥሎ ሊሰራ ይገባል ብለው የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የተሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የስር መዋቅሮች አፈጻጸምን በሚገባ መከታተል ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል።

ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ በመሆን በሙስና በሌሎች ህዝቡን ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ፍትሃዊ ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

በይገባኝ የማይሻሩ ውሳኔ ከመስጠት አኳያ የተሰሩ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለው አማራጭ ሙግት መፍቻ ስርዓትን ለማጠናከር እና ለህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተካሄደበት አግባብ ጥሩ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ነፃ የህግ ድጋፍ፣ ምክር፣አገልግሎትና ንቃተ ህልና ትምህርት በመስጠት የተሰሩ ስራዎች በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራርን የበለጠ በማጠናከር በህዝቡ ዘንድ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮችን በተገቢ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

የክልሉ ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሴቶችና ህፃናት ቢሮን፣ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮን የ2017 አፈጻጸምን የገመገሙ ሲሆኑ ከቋሚ ኮሚቴዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ከቢሮ ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እያከናወነ ያለው ስራዎች አበረታች መሆኑን የክልሉ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ገለጸ