Seble
Wed, 07/16/2025 - 17:27
መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 9/2017)፣ መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።
የመከላከያ ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ ተካሂዷል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት፥ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በመከላከያ በኩል 18 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሠራዊት ተተክለው፣ ለምግብነት የደረሱ የብርቱካን፣ ሎሚ፣ ሮማን፣ ፓፓዬና ሌሎችም ፍራፍሬዎች ለአባላቱ እየቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እንደ ሀገር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የደን ሽፋንን በማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ውጤት እያመጣ መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
Image
