Seble
Wed, 07/16/2025 - 17:33
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነዉ፣
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 9፣ 2017፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛል።
ጥናቶቹ ከተሞችንና ከተሜነትን በዘመነ መንገድ በመምራት ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስለመሆናቸዉ ተገልጿል ።
የጥነት ሠነዶቹ በከተምች ፈርጅ ሽግግሮችን ፣ በከተማ ተቋማዊ አደረጃጃትና አሠራሮች ማሻሻያዎችን እና ፣በከተሞች ከመሬት ጋር የተያያዙ ህገዎጥነቶችን በመከላከል ዙሪያ ያተኮሩ ሲሆን የጥናት ሠነዶቹ ቀርበዉ ዉይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
Image
