Skip to main content

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በሀብት አጠቃቀምና አስተዳደር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዘገቡን የክልሉ ምክር ቤት የክልሉ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ

(ሆሳዕና፦ሀምሌ 9/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፋይናንስ ቢሮ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።

የክልሉ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስትን ሀብት በማስተዳደር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዘገቡን ተናግረዋል።

በራስ አቅም ከዕዳ ነፃ በመሆን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግና የውስጥ ሀብትን በመሰብሰብ የክልሉን ልማት ለማፋጠን በርካታ ስራዎች መሰራቱን በመግለፅ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

በሀብት አጠቃቀምና በፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን በማስፋን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው ብለው በቀጣይ የህዝብ ተጠቃሚነቱ የበለጠ እንዲጎላ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል።

ብልሹ አሰራሮችን በመለየት የሀብት ብክነትን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች አበራታች ስለመሆኑ ገልፀው ስርዓቱን እስከ ታችኛው መዋቅር በመዘርጋት የአሰራር ጥሰቶች እንዳይኖር አበክረው እንዲሰሩም አሳስበዋል።

ከተለያዩ የልማት  ፕሮጀክቶች ጋር በቅንጅት በመስራት የተመደበውን በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የተሰራው ስራ ለቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የክልሉን በጀት ዝግጅትና አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር በሁሉም አስተዳደር እርከኖች ፍትሃዊ ሀብት ክፍፍል እንዲኖር የተደረገበት አግባብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የገቢና ወጪ ክፍተት ለመሸፈን የተሰሩ ስራዎችን የበለጠ ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ ታመነ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ታመነ ተናግረዋል።

የመደበኛ በጀት አሰባሰብ እና አጠቃቀምን እስከ ታችኛው መዋቅር ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳከት የተሰሩ ስራዎች አበረታች እንደሆነ ገልፀዋል።

የሂሳብ ሪፖርት ወቅታዊነትና ተደራሽነት ላይ የሚሰሩ ስራዎች በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለው ተቋሙን በተለያዩ ቴክኖሎጂ የማዘመን ስርዓትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ከኦዲት ግኝትና ዕዳ አመላላስ ሂደት ጋር የሚታዩ ክፍተቶችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በማረም በጥራት እንዲሰራና የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት ለቀጣይ በጀት  ዓመት በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልገሎት እንዲሰጥ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ለማረም ወደ ስራ መግባት ይጠበቃል ብሏል።

በተመሳሳይ ሰዓት የክልሉ  ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትምህርት ቢሮን፣ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮን የ2017 አፈጻጸምን የገመገመ ሲሆን ከቋሚ ኮሚቴዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች  ከቢሮ ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በሀብት አጠቃቀምና አስተዳደር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዘገቡን የክልሉ ምክር ቤት የክልሉ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ