Skip to main content

በህዝቦች መካከል አብሮነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተመላከተ

ሆሳዕና ፦ሀምሌ 10/2017የማረቆ ልዩ ወረዳ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ማቋቋሚያ የአይነት ድጋፍ አድርጓል

የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ እንደገለጹት  ከዚህ ቀደም የምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ለማጠናከር በገቡት ቃል መሰረት አስር ሰንጋዎች  ቡታጅራ ከተማ በመገኘት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ድጋፉ ለወንድም እህት ወገን ለሆኑ ለዞኑ ማህበረሰብ አብሮነታችን ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ዞኑን ለማቋቋምና የተሻለ አገልግሎት ለማህበረሰቡ እንዲሰጥ በሚደረገው ጥረት ልዩ ወረዳው  በቀጣይ መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ  የአብሮነታችንና አንድነታችን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣይም ሁለቱ መዋቅሮች በመዳጋገፍና በመተባበር የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በምስራቅ መስቃንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አካባቢ የተፈጠሩ ግጭቶችን በክልሉ አመራር ቆራጥ ውሳኔ ሰጪነትና በሁለቱም መዋቅር አመራሮች በጋራ በመስራት ወደተሻለ ሰላም መምጣቱን አንስተው በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
በህዝቦች መካከል አብሮነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተመላከተ