Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት እና  አስፋልት መንገድ ስራ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው

(ሆሳዕና ፣ሐምሌ 10/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ከሀዲያ ዞን እና ከሆሳዕና ከተማ አመራሮች ጋር በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት እና  የአስፋልት መንገድ ስራ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው።

በመድረኩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ተገኝተዋል።

በሆሳዕና ከተማ ግንባታው እየተካሔደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ከፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ጋር ተቀናጅቶ ተፈጻሚ መሆን በሚችልበት ጉዳይ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እየገመገሙ ነው።

በክልሉ 165 ኪ/ሜ የኮሪደር ልማት ግንባታ ለማካሔድ እየተሰራ መሆኑ ይታወሳል።

ምንጭ :-. የክልሉ መ/ኮ

Image
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት እና  አስፋልት መንገድ ስራ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው