Skip to main content

ባሳለፍነው በጀት አመት የክልሉ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና የጋራ እሴቶቻቸውን እንዲያጎለብቱ በልዩ ትኩረት ተሰርቷል- አቶ አቡቶ አኒቶ  

(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 10/2017)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ባሳለፍነው በጀት አመት የክልሉ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ ከመጠቀም ባለፈ የጋራ እሴቶቻቸውንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን  እያጎለበቱ እንዲሄዱ በልዩ ትኩረት መሰራቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ ተናግረዋል ።

አቶ አቡቶ የምክር ቤቱ  3ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲካሄድ እንዳሉት ምክር ቤቱ የህዝቦችን ህገ መንግስታዊ መብቶች ከማስጠበቅ ባለፈ በጋራ እሴቶች መጎልበት፣ በሰላማዊ ግንኙነትና መስተጋብር፣ በህዝቦች አንድነት፣ የመብትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማረጋገጥ  ረገድ ግቦችን አስቀምጦ ሲሰራ ቆይቷል።

በህገ  መንግሥትና ፌደራላዊ አስተምህሮ የህዝቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ጥረት መደረጉን ያነሱት አቶ አቡቶ የክልሉ በጀት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ብለዋል።

በክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እና ሌሎችም አመራሮች ተገኝተዋል።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
ባሳለፍነው በጀት አመት የክልሉ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና የጋራ እሴቶቻቸውን እንዲያጎለብቱ በልዩ ትኩረት ተሰርቷል- አቶ አቡቶ አኒቶ