Seble
Thu, 07/17/2025 - 12:37
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አባላት በሳጃ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
(ሆሳዕና፣ሀምሌ 10/2017) ፣በምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ ሳጃ ከተማ የሚገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አባላት በከተማዋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣የየም ዞንና የሳጃ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል።
ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ
Image
