ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አገልግሎቱን በማዘመን የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየሰራ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ
(ሆሳዕና፦ ሀምሌ 10/2017) የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።
የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ ቢሮው በከተሞች ልማት እየሰራ ያለው ተግባር አበረታች ነው ብለዋል።
በከተሞች ኮርደር ልማት የተሰሩ ስራዎች አበረታች እና የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ በመሆኑ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ተጠናቅቆ ለህዝቡ አገልገሎት እንዲሰጥና ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።
የሚሰሩ የልማት ተግባራት በስታንዳርድና በጥራት እንዲገነቡ ልዩ ድጋፍና ክትትል ያስፈልጋል ብለው በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የሚሰሩ ኢኒሼቲቭ ጥሩና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በከተሞች የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሰራ ያለው አበራታችና ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
የመዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና የከተማ ፕላን ዝግጅት እንዲሁም የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ስራዎች የሚሰሩ ተግባራት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በከተሞች መሬት ይዞታ ምዝገባ ስራዎች እና የመሬት ልማት አስተዳደር አፈጻጸም መልካም ስራዎች ብሰሩም የህዝብን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር ተጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ታመነ ተናግረዋል።
በኮንስትራክሽን ዘረፈ የተሰሩ ስራዎች አበራታች ነው ብለው የፅዱ ከተማ ሞዴል መፀዳጃ ቤት፣የክልል ቢሮ ህንፃዎች ግንባታ እና ሌሎች የተጀመሩ ተግባራት ቶሎ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
በተመሳሳይ ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቢሮን የ2017 አፈጻጸምን የገመገመ ሲሆኑ ከተመላላሽ ቋሚ ኮሚቴዎችና ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥያቄዎች ከቢሮ ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
