የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች የሚበረታታ መሆኑን የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ
(ሆሳዕና፦ ሀምሌ 10/2017) የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።
ቢሮው አሰራርን በቴክኖሎጂ በማዘመን የህዝብን የመልካም አስተዳደር ቅሬታን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ነው ብለው የቁጥጥር ስርዓቱ በማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
በጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ግንባታዎችን በማፋጠን የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።
ትርፍ መጫንና ከታሪፍ በላይ መጫንን ለማስቀረት የስምሪት መስመሮችን በኢትኬትንግ አገልግሎት እንዲሰጥ እየተደረገ ያለው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።
የትራንስፖርት አገልግሎት ደህንነቱን የጠበቀ እንዲሆን የሚሰሩ ተግባራት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለው በትራፊክ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የትራንስፖርትና መንገድ መሰረተ ልማትን ፍትሃዊና ተደራሽ በማድረግ ለህዝብ ተጠቃሚነት በልዩ ትኩረት መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በመንገድና ድልድይ ግንባታ እና በመንገድ ጥገና ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክሮ እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።
ለስምሪት ብቁ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎች ስምረት እየተሰጠ በመሆኑ በህዝብና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የቁጥጥር ስራዎች መጠናከር ያስፈልጋል ነው የተባለው።
የደረቅ ጭነት መናኸሪያ አካባቢ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀው በህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ እየተሰሩ ያሉ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ትላልቅ የመንገድ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ በቅንጅትና በልዩ ትኩረት እንዲሰራም ነው አቶ ታመነ ያሳሰቡት።
ከተመላላሽ ቋሚ ኮሚቴዎችና ከቋሚ ኮሚቴ ለተነሱ ጥያቄዎች ከቢሮ ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
