የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሰላም ተምሳሌትነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በቅንጅት የተሰራው ስራ አበራታች መሆኑን የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ
(ሆሳዕና፦ ሀምሌ 10/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ቸወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰላምና ፀጥታ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።
የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እንደገለፁት ቢሮው የሰላም ተምሳሌትነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በቅንጅት የተሰራው ስራ አበራታች መሆኑን ገልፀዋል።
ቢሮው የክልሉን የሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጦችን ለማስመዝገብ ተችሏል ነው ያሉት።
የመረጃ ስርዓቱን በማጠናከር የግጭት፣ የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን የገለፁት ወ/ሮ መሰረት በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
በክልሉ የፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት፣ በመቆጣጠር እና በመከላከል አበራታች ተግባራት ስለሚከናወኑም ተናግረዋል።
በማህበረሰቡ ውስጥ ለሰላም እሴት ግንባታ የሚረዱ የሰላም አደረጃጀቶች ጋር የተሰሩ ስራዎች ጥሩ በመሆኑ ለቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።
የሰላም፣የአብሮነት እና የብዝሃነት እሴቶችን በማጎልበት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በመፍጠር የተሰሩ ስራዎች አበራታች መሆኑን ገልፀዋል።
የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀልን ለመከላከል የተተገበሩ ተግባራት እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሳዊ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ግንባታ በተሰሩ ስራዎች በወንጀል መከላከል ላይ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
ከአጎራባች ክልሎችና ድንበር አካባቢዎች የማህበረሰብን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ርብርብ መደረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት በመቆጣጠር እና በመከላከል ረገድ እንዲሁም በህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉም ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል።
የወሳኝ ኩነት የምዝገባ ሽፋንን ተደራሽ በማድረግና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም በቀጣይ የሚሰሩ እና የቀሩ ተግባራት በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ከተመላላሽ ቋሚ ኮሚቴዎችና ከቋሚ ኮሚቴ ለተነሱ ጥያቄዎች ከቢሮ ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
