የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ከሐምሌ 16 እስከ 18 /2017 እንደሚካሄድ ገለፀ
(ሆሳዕና፦ ሀምሌ 11/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ጉባኤውን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከጉባዔው በፊት ቅድመ ጉባዔ በከተማ ሥራዎች ላይ የሁለት ቀናት የመስክ ጉብኝት እንደሚደረግ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ጠቁመዋል።
ጉባዔተኛው ሐምሌ 13/2017 ቡታጅራ ከተማ ገብቶ በማደር ሐምሌ 14 እና 15 በተለያዩ ከተሞች በሚደረጉ የመስክ ጉብኝቶች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ከሐምሌ 16 እስከ 18/2017 ድረስ የምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ወልቂጤ ላይ የሚካሄድ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ገልፀዋል።
በጉባዔው ከምክር ቤት አባላት በተጨማሪ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ ስለመሆናቸው ገልፀዋል።
በጉባኤውም የ2017 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ አካላት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አፈፃፀም ሪፖርት እና ተያያዥ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት የሚደረግ ይሆናል ነው የተባለው
ለጉባዔው የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ በመሆኑ የምክር ቤት አባላትም በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በተላለፈው ጥሪ መሰረት በተጠቀሰው ቦታ እና ጊዜ እንዲገኙ ዋና አፈ ጉባኤዋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
