Seble
Mon, 07/21/2025 - 11:12
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቡታጅራ ከተማ የልማት ፕሮደክቶችን ምልከታ እያደረጉ ነው
ሆሳዕና፣ሐምሌ 14/2017)የምክር ቤቱ አባላት በከተማዋ እየተነገባ ያለውን የኮሪደር ልማት፣የከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ፣የክልል ተቋማት የግንባታ ፕሮጀክቶች፣የማህበረሰብ አቀፍ መድሀኒት ቤት፣የአረንጓዴ መናፈሻ ስፍራዎችን እና ሌሎች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት አውታሮችን እየተመለከቱ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ መንግስት የተቀረጹት በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የልማት ስራዎች ውጤታማ ናቸው።
በከተሞች እየተገነቡ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ፕሮጀክቶችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ገንብቶ የማጠናቀቅ ልምድ ማዳበር የተቻለበት ስለመሆኑ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
የምክር ቤቱ አባላት እንደ ሀገር "በመትከል ማንሰራራት"በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሔደውን የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለማጠናከር በቡታጅራ ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
Image
