Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወራቤ ከተማ የልማት ፕሮደክቶችን ምልከታ እያደረጉ ነው

ሆሳዕና፣ሐምሌ 14/2017)የምክር ቤቱ አባላት በወራቤ ከተማ  የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች ህንጻ ግንባታ፣ የወራቤ ሶጃት የኢንዱስትሪ መንደር፣የወንዝ ዳር ልማት፣ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን እየተመለከቱ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በዚሁ ጊዜ  እንደገለጹት አመራሩ ማህበረሰቡን በማስተባበር በልማት ስራዎች ላይ ከተጋ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የወራቤ ኢንዱስትሪ መንደር አመላካች ነው ብለዋል።

የወራቤ ኢንዱስትሪ መንደር ለእርሻ አገልግሎት የማይውል ድንጋያማ አካባቢ መሆኑን የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤዋ ይህን ወደ ልማት በመቀየር መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ገለጻ የወራቤ ሶጃት የኢንዱስትሪ መንደር በራስ አቅም እየተገነባ ነው ብለዋል።

ሶጃት የወራቤ ኢንዱስትሪ መንደር  በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በሀገሪቱ ኢኮንሚ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

በዞኑ ለወራቤ ሶጃት የኢንዱስትሪ መንደር 1ሺ ሄ/ር መሬት የተከለለ ሲሆን 406ሄ/ር መሬት ወደ ልማት ገብቷል።

በኢንዱስትሪ መንደሩ 23ቢሊየን ብር ካፒታያ የተመዘገበ ሲሆን 5 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በስራ ላይ ስለመዋሉ ተመላክቷል።

በኢንቬስትመንት የተሰማሩ 163 ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ግንባታቸው የተጠናቀቀ 34 ናቸው።

በኢንዱስትሪ መንደሩ ለ5ሺ 482 ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ

Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወራቤ ከተማ የልማት ፕሮደክቶችን ምልከታ እያደረጉ ነው