የሴቶች እና ህጻናት ጥቃት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል እንደሚመለከት ተገለፀ ።
###########################
(ሀምሌ 15/2017 Uለባ) የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሴ/ህ/ ልዩ የም/ ክስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በዩኒሴፍ በመደገፍ የVAC, ECM/FGM እና one stop center የ2017 በጀት ዓመት የፕሮግራም አፈፃፀም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ገመገመ።
በዕለቱ መድረኩን በይፋ የከፈቱት የቢሮ የሴ/ህ/ ልዩ የም/ ክስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አፈወርቅ ደምሴ በንግግራቸው ፍትህ ቢሮ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በመወጣት ክልሉ በሴቶች እና ህጻናት በሚፈፀሙ ጉዳቶች ዙሪያ የተለያዩ ማዕከላትን በማቋቋም እየሰራ ይገኛል በማለት የገለጹ ሲሆን በዛሬ የወይይት መድረካችንም በ 2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት በጋራ የምንገመግምበትና በድክመት ያሉብንን ጉዳዮች በመለየት ጥንካራችንን በማስቀጠል እና በድክመቶቻችን ዙሪያ ወይይት የምናደርግበት ይሆናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመቀጠል ከልዩ ወረዳ ፣ ከወረዳ እና በከተማ ማዕከላት በ 2017 በጀት ዓመቱ የተሰሩ አበይት ስራዎች ዙሪያ በባለሙያዎች ሪፖርተ የቀረበ ሲሆን እንደ ክልልም የድጋፍ ክትትል ሪፖርትም በአቶ አፈወርቅ ደምሴ ከቀረበ በኋላ ከቤቱ በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ጥያቄ እና አስተያየት በሰፊው ከተነሳና ምላሽ ከተሰጠባቸው በኋላ በቀጣይ በጀት አመት በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የቢሮው መ/ኮ ነው
