Skip to main content

የክልሉ መንግስት በሀገር ደረጃ የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት ሁሉን አቀፍ ጥረት እያደረገ ነው - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር

ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት 2018 ዓ/ም ከተስፋ ብርሐን ወደሚጨበጥ ተስፋ የምንሸጋገርበት ነው ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተስፋ ብርሀን እያየን መጥተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በ2018 የተስፋ ብርሐኑ የሚጨበጥ እንደሚሆን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በጽኑ መሰረት ላይ የሚገነቡበት መሆኑንም አመላክተዋል።

በ2023 ኢትዮጵያ ብልጽግናን መሰረት አድርጋ የአፍሪካ ተምሳሌት እንድትሆን በሀገር ደረጃ ራዕይ ሰንቀን እየሰራን ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በ2040 ደግሞ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የብልጽግና አርአያ መሆን የምትችል ሀገር ትሆናለች የሚል ግብ ስለመቀመጡም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

በክልሉ የተመዘገቡ ውጤቶች በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ያጋጠሙ አደናቃፊ ጉዳዮች በፓርቲና በመንግስት የላቀ ጥረት መሻገር መቻሉን ጠቁመዋል።

ወደፊት ለሚገጥሙን ተግዳሮቶች በመፍትሄነት  የተቋም ግንባታ እና የአሰራር ስርዓትን ማዘመን ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

ምንጭ የክልሉ መ/ኮ

Image
የክልሉ መንግስት በሀገር ደረጃ የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት ሁሉን አቀፍ ጥረት እያደረገ ነው - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር