Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ለ2018 በጀት ዓመት 43 ቢሊየን 252ሚሊየን 509ሺ 909 ብር አጸደቀ

ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ለ2018 በጀት ዓመት 43 ቢሊየን 252 ሚሊየን 509ሺ 909 ብር አጸደቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ተወያይቶ አጽድቋል።

በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ ለምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ የበጀት አዋጅ አቅርበዋል።

በጀቱ ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች መደበኛ እና የካፒታል ወጪ፣ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች ጥቅል በጀት፣ለክልላዊ ፕሮግራሞች፣ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ፣ለክልሉ መጠባበቂያ መሆኑን ነው አቶ ታመነ በረቂቅ አዋጁ የጠቆሙት።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም የ2018 በጀት አስመልክቶ ለምክርቤቱ በዝርዝር አቅርበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2018 የቀረበውን በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ምንጭ የክልሉ መ/ኮ

Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ለ2018 በጀት ዓመት 43 ቢሊየን 252ሚሊየን 509ሺ 909 ብር አጸደቀ