በክልሉ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር ህብረተሰቡ ከ1ቢሊየን 602ሚሊየን በላይ ሀብት ድጋፍ አድርጓል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳስታወቁት
ህብረተሰቡ ከ1ቢሊየን 602ሚሊየን 648ሺ 405 ብር በገንዘብ፣በአይነት እና በጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
ይህን ተከትሎም 39 አዳዲስ የቅድመ -አንደኛ ፣30የመጀመሪያና መካከለኛ እንዲሁም 5 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማከናወን ስለመቻሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
የክልሉ ህዝብ ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ የላቀ ተሳትፎ ማበርከቱን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
በትምህርት ዘመኑ ከክልሉ መንግስት የበጀት ድጋፍ በተጨማሪ የማህበረሰብ አቀፍ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተግባራዊ መደረጉን ጠቁመዋል።
በ82 ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በ259 ትምህርት ቤቶች ከ62ሺ በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
የምገባ ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ፣የልማት አጋር ድርጅቾች እና ባለሀብቶች የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
