Skip to main content

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 62ሺ 799 መዛግብት ውሳኔ አግኝተዋል - የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት

ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት  ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በወንጀል እና በፍትሀብሔር  62ሺ 799 መዛግብት ውሳኔ አግኝተዋል።

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ በወንጀል እና በፍትሐብሔር ከቀረቡት ጉዳዮች ውስጥ 1ሺ 976 መዛግብት ወደ ቀጣዩ ዓመት ተላልፈዋል።

የፍርድ ቤቶች ውጤታማነትና ቅልጥፍና ከሚለካባቸው ዘዴዎች ውስጥ አንዱ የመዛግብትን የማጥራት አቅም ከፍ አድርጎ መገኘት ስለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።

የፍርድ ቤቶች ውጤታማነት የሚለካው ተገማችነት፣ወጥነት ያለው፣በተወሰነው ጊዜና ጥራቱን የጠበቀ ውሳኔ በመስጠት እና የህብረተሰቡን እርካታ ከፍ በማድረግ  የሚኖረውን አመኔታ እንዲጨምር መስራት  መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።

በይግባኝ የማይሻር ውሳኔ መስጠት በፍርድ ቤቶች ውጤታማነት ከፍተኛ ስፍራ እንደሚሰጠውም ፕሬዝዳንቱ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

በክልሉ ፍርድ ቤቶች በባህላዊ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች በወንጀል እና በፍትሐብሔር 5ሺ 343 ጉዳዮችን በዕርቅ እልባት እንዲያገኙ መደረጉን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።

በክልሉ የህግ ግንዛቤ ለሌላቸው ለ25ሺ አቅመ ደካሞች፣ህጻናት፣ሴቶች እና አረጋውያን ነጻ የህግ ድጋፍና  የምክር አገልግሎት ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ስራ ማስፈጸሚያ የሚውል 81ሚሊየን 656ሺ 347 ብር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 62ሺ 799 መዛግብት ውሳኔ አግኝተዋል - የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት