Skip to main content

ትምህር ቤቶች የአገልግሎት መስጫ ተቋም ብቻ ሳይሆኑ ትውልድ የሚቀረጽባቸውና የሚገነባባቸው ናቸው - አቶ አንተነህ ፍቃዱ

(ሆሳዕና፦ሀምል 18/2017) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የግልና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤት ባለቤቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ምስረታ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለፁት የግልና መንግስታዊ  ያልሆኑ ትምህርት ቤት ባለቤቶች ማህበር ምስረታ የጋራ ርዕይ የሚጀመርበት ነው ብለዋል።

የጋራ ርዕዩም ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጋራ አመራር መስጠትና ፍትሃዊ የሆነ ትምህርት አሰጣጥን በክልሉ ማረጋገጥ ስለመሆኑም ገልፀዋል።

ትምህር ቤቶች አገልግሎት መስጫ ተቋም ብቻ ሳይሆኑ ትውልድ የሚቀረጽባቸውና የሚገነባባቸው ቁልፍ ተቋማት ናቸው ብለዋል።

የግልና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች ለመንግስት ትምህርት ቤቶች አጋር በመሆን ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ነው ያሉት።

በመድረኩም የግል ትምህርት ተቋማት ተወካዮች፣ የክልል ፣ የዞንና ልዩ ወረዳ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ

Image
ትምህር ቤቶች የአገልግሎት መስጫ ተቋም ብቻ ሳይሆኑ ትውልድ የሚቀረጽባቸውና የሚገነባባቸው ናቸው - አቶ አንተነህ ፍቃዱ