Seble
Tue, 07/29/2025 - 09:56
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
(ሆሳዕና ፣ሐምሌ 21/2017)2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባዔው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ እንዲሁም የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ተገኝተዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ፣ የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዚዳንት አልቫሮ ላሪዮ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ፣ በርካታ ሚኒስትሮች እና ባልድርሻ አካላት በጉባዔው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ጉባዔውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከጣሊያን ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ (Rai) ጋር በመተባበር በተለያዩ አማራጮች ለአድማጭ ተመልካቾች እያደረሰ ይገኛል።
ኢቢሲ
Image
