Seble
Tue, 07/29/2025 - 10:38
ከ100 ሺህ ቶን በላይ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋለ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ
(ሆሳዕና፣ሀምሌ 23/2017)፣ በአዲስ አበባ በዓመት ከመነጨው 100 ሺህ 585 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
በከተማዋ 325 የመልሶ መጠቀም ማህበራት የተቋቋሙ ሲሆን በዓመት ከተመረተው 983ሺህ 944 ቶን ቆሻሻ 100 ሺህ 585 ቶኑን መልሰው ጥቅም ላይ ማዋላቸውን አስታውቀዋል።
አምስት ሺህ 460 ቶን ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ስራ ማዋል ተችሏል ብለዋል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ በጽዳት ዘመቻው 675 ሺህ 384 ነዋሪዎችና ሁለት ሺህ 540 ተቋማት በሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተሳትፈዋል ።
በአጠቃላይ በተሰራው የጽዳት ስራ በከተማዋ የሚከሰቱ የወረርሽኝ ምጣኔዎችን መቀነስ፣ ወንዟችና አካባቢን ከብክለት መታደግ፣ ቆሻሻን ወደሀብት መቀየር እና ከተማዋን ውብና ጽዱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ቆሻሻን ከመሰብሰብ ባለፈ በአግባቡ የማስተዳደርና መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ
Image
