Skip to main content

የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተመላከተ

(ሆሳዕና ፣ሀምሌ 22/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆልት አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበር በተሻሻለው በአዲሱ አማራጭ የህፃናት ድጋፍና ክብካቤ መመሪያ ላይ የተዘጋጀ  በሆሳዕና ከተማ እየተሰጠ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ እንዳሉት ህፃናት ላይ የሚሰራው ስራ ሀገር ላይ መስራት ነው።

የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ያሉት ኃላፊዋ በህፃናት ላይ የሚደረገው ድጋፍና ክብካቤ ይበልጥ መጠናከር እንዳለበትም አመላክተዋል።

በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ የወጣው አማራጭ የህፃናት ድጋፍና ክብካቤ መመሪያ በህፃናት ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመከላከልና ተጋላጭነታቸውን በመቀነስ ህፃናት ወደ ጎዳና እንዳይወጡ ለማድረግ በማለም የተዘጋጀ መመሪያ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

መመሪያው የህፃናት መብትና ደህንነት እንዲረጋገጥና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የገለፁት ወ/ሮ አምሪያ በመመሪያው የፈፃሚና የአስፈፃሚ አካላት ግንዛቤ ከፍ እንዲል በተለያዩ ማዕከላት ስልጠናው  በተደራጀ  መልኩ መሰጠቱን ገልፀዋል።

በህፃናት ላይ የሚሰራው ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በመተባበር ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

ስልጠናው በተደራጀ አግባብ እንዲሰጥ ሆልት አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ከፍተኛ አሰተዋጽኦ ማበርከቱን ከክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተመላከተ