Skip to main content

የዘንድሮው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት የሚከበር ነው - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

ነሐሴ 5፣ 2017  የዘንድሮው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት የሚከበር ነው አሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን በተመለከተ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት የዐቢይ ኮሚቴ አባላት የመጀመሪያውን የመሪ ዕቅድ ውይይት እያካሄደ ነው።

አፈ ጉባኤ አገኘሁ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበር መሆኑ የለውጡ መንግስት ጥያቄን የመመለስ ተግባራዊ ትሩፋትን የሚያሳይ ነው።

ቀኑ በልዩ ድምቀት የሚከበር መሆኑን አንስተው÷ ለዓመታት በልሂቃን መካከል ሲስተናገድ የነበረው ከፍተኛ የልዩነት ችግር ለመፍታት እንደ ሀገር ምክክር የሚደረግበት መሆኑን ጠቁመዋል።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ኅዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል።
(ኤፍ ኤም ሲ)

Image
የዘንድሮው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት የሚከበር ነው - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር