Skip to main content

በአፍሪካ ትልቁ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በቢሾፍቱ

ከ75 ዓመታት  በላይ አፍሪካን ከዓለም ያገናኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጠቀምበት የቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅሙ በዓመት እስከ 25 ሚሊዮን የደረሰ ቢሆንም፤ እያደገ ያለውን የአቪየሽን ፍላጎት ማሟላት አልተቻለም።

ይህን ፍላጎት ለማሟላትም ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፤ በ10 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያን ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

አዲሱን የአውሮፕላን ማረፊያ መገንባት እያደገ ያለውን የአቪዬሽን ዘርፍ ፍላጎት ለሟሟላት፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና ሀገሪቱ በአቪየሽን ዘርፍ መሪነቷን አጠናክራ እንድትቀጥል ያስችላል ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ።

ፕሮጀክቱ የአውሮፕላን ማረፊያ ብቻ ሳይሆን፣ የፓና አፍሪካ ትስስርን ለማጠናከር፣ ለኢኮኖሚ ፣ለቱሪዝም እና ለንግድ እድገት እንዲሁም ለባህል ልውውጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል። (ኢቢሲ)

Image
በአፍሪካ ትልቁ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በቢሾፍቱ